ጥቂት ስለኮሮና ቫይረስ
----------------------------
ኮሮና ቫይረስ "እኛን አይዘንም፣ ጥቁርን አያጠቃም" ብሎ መዘናጋት፣ ራሱን ቫይረሱ እንዲንሰራፋ ይጠቅመው ካልሆነ በቀር፣ ሌላ ማንንም አይጠቅምም። "ሊይዘን ይችላል" ብሎ ከልክ በላይ መራድም ምንም አይጠቅመንም። ይልቅስ መተላለፊያ መንገዶቹን እና የቫይረሱን ባህርይ ጠንቅቀን ለማወቅ መጣር፣ ለሌሎች ማሳወቅ፣ በምንችለው ሁሉ ራሳችንን እና አካባቢያችንን እየጠበቅን፣ በየእምነታችን ፈጣሪ እንዲያርቅልን፣ ቶሎ መቆጣጠር እንዲቻል፣ ጥበቡን ለሰው ልጆች እንዲሰጥና መዳኛው ወይ ክትባቱ ቶሎ እንዲገኝ መጸለይ ነው።
የሚተላለፈው እንዴት ነው?
---------------------------------
ከታመሙ ሰዎች ጋር ቅርብ ንክኪ በማድረግ
ከታመምን ምልክቶቹ መች ይታያሉ?
-------------------------------------------
ከ2-14 ባሉ ቀናት ውስጥ
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
-------------------------------
ትኩሳት፣ ስል እና የትንፋሽ ማጠር ወይም ለመተንፈስ መቸገር ናቸው።
ራሳችንንም ሌሎችንም ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንችላለን?
-----------------------------------------------------------------------
፩) እጅን በሳሙና ለሃያ ሰከንዶች ያህል በደንብ መታጠብ። (ለምሳሌ የበር እጀታ ወይም ስልካችንን ነክተን ቢሆን፣ መታጠብ።)
እጅ መታጠብ ቀዳሚው እና ወሳኙ ነው። ጉንፋንም ቢሆን በዋናነት በእጅ አማካኝነት ነው የሚተላለፈው።
፪) እጃችንን መታጠብ በማንችልበት ሁኔታ እና፣ የጸረ ተዋህስያን ፈሳሽ (sanitizers) ማግኘት ከቻልን እነሱን መጠቀም። ነገር ግን እጅ መታጠብ ሁሌም የተሻለ አማራጭ ነው።
፫) ባልታጠበ እጅ፥ አፍንጫ፣ አይን እና አፍን አለመንካት። እጃችንን ከፊታችን መሰብሰብ።
፬) በተቻለ መጠን መተዛዘሉን በመቀነስ የየራሳችንን ቦታ ለማግኘት መሞከር (having some space)
፭) ከታመሙ ወይም ምልክቱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ። በሩቁ መሆን።
፮) በአጠቃላይ የጉንፋን ዓይነት ስሜት ሲሰማን፣ ራሳችንን ካልታመሙ ሰዎች ማራቅ።
፯) እጃችን የሚያርፍባቸውን ቦታዎች ማጽዳት። ስልካችንን ጨምሮ።
፰) በምናስነጥስበት ጊዜ ሶፍት ወረቀት ወይም ክንዳችንን መጠቀም
፱) ከተቻለ ቫይረሱ ያለባቸው አካባቢዎች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱና ቤት እንዲቆዩ ማድረግ
ምክልቶቹ ከታዩን
---------------------
፩) ከቤት አለመውጣት
፪) በምናስነጥስበት ጊዜ ሶፍት ወረቀት ወይም ክንዳችንን መጠቀም
፫) እጃችን የሚያርፍባቸውን ቦታዎች ማጽዳት። ስልካችንን ጨምሮ።
፬) አፍንጫና አፋችንን የሚሸፍን ማስክ መጠቀም።
በአጠቃላይ
--------------
በየእምነታችን ጸሎት! የማናምንም የስበት ኃይልም (law of attraction) ቢሰራልን፣ ጥብቅ መልካም ምኞት ማድረግ!
በርግጥ አገራችን ውስጥ ከላይ ያሉትን ለማድረግ ሁኔታዎች ከባድ እንደሆኑ ይታወቃል። ይያዝልን እያልን መጸለይ ዋናው ነው።
መልእክቱን ለሌሎች SHARE እናድርግ!