የኮሮና ቫይረስ እንዳይሰራጭ የምንችለውን ሁሉ ጥንቃቄ ስናደርግ መረጋጋትን እና ሌሎችን አለማግለልን በማስቀደም መሆን አለበት። አሁን ሁሉንም ቁጥር፣ ሁሉንም መረጃ በየሰዓቱ ማየት የምንችልበት ጊዜ ስለሆነ ይጋነናል እንጂ፣ የሰው ልጆች በታሪካቸው ብዙ ነገሮችን አሳልፈዋል። ስኬት በተቀዳጁባቸው ጊዜያት ሁሉም፣ ኅብረት እና እርስ በእርስ መደጋገፍ፣ መመካከር ነበራቸው። ይህንንም በጋራ ትብብር እና ድጋፍ በፍቅር እና በእርጋታ ትክክለኛ መረጃዎችን በመቀባበል እናልፈዋለን።
ለመከላከል እጃችንን በሳሙና መታጠብ ቀዳሚው ነው። ባልታጠበ እጅ ፊታችንን አለመንካት። የምንጠቀምባቸውን እና የምንነካቸውን እቃዎች (ስልካችንን ጨምሮ) ንጽህና መጠበቅ። የህመሙ ምልክቶች (ሳል፣ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር) ካሉባቸው ሰዎች ጋር ያለንን ቅርርብ በጥንቃቄ ማድረግ ነው።
ይሄ ማለት የታመሙትን ማግለል ማለት ሳይሆን፣ የታማሚው ቁጥር ከበዛ አስታማሚ እንዳይቸግር በማሰብ ጭምር ለእነሱም ለራሳችንም ስንል ነው። እንጂ እኛ ኖረን ከጎናችን ያሉ ባይኖሩ መኖሩስ ምኑን መኖር ይሆናል? ነገሩን ልበል እንጂ የመግደል እድሉ በጣም ትንሽ ነው። በምናስነጥስበት እና በምናስልበት ጊዜም ክንዳችንን መጠቀም፣ ወይም መሀረብ እና ሶፍት መጠቀም ያስፈልጋል። የህመሙ ምልክቶች ካልታዩ በቀር ማስክ መጠቀም አያስፈልግም።
(ከእነዚህ ውጭ ያሉ መረጃዎች ስንሰማ ከዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት፣ ከጤና ጥበቃ ሚንስትር ወይም ሌላ ታማኝ ድርጅት ማመሳከር ያስፈልጋል።)
በተረፈው በየእምነታችን ጸሎት እናድርግ። የማናምንም ለሰው ልጆች ጥበብን የሚገልጽ ሀይል አለ ብለን መልካም ምኞታችንን በልባችን እናድርግ።
ለሌሎች SHARE እናድርግ!