ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ❤ በ96 አመታቸው አርፈዋል!
እንደ እናት አፍቅረውን አገልግለውናል። እንኳን በዚህ ክፉ ወረርሽኝ የመጣ ነጮችን ስናገል እና ስናሳድድ አይተው ሳያዝኑብን አረፉ። 😔
በሕይወቴ ከሰራኋቸው ጠብታ ነገሮች መካከል፣ በልደት ቀኔ ለእርስዎ እና በእርስዎ ጥላ ሥር፣ ድጋፍ ፍቅር እና እንክብካቤ ለሚያገኙ ሴቶች፣ ልባዊ ሰላምታና ፍቅር ለመላክ ብዬ ጥቂት ገንዘብ ከወዳጆቼ ሰብስቤ መላኬ አንዱ ነው።
በዚያ ሰሞን ችግኝ ትተክሉ ነበርና፣ በስሜ በፍቅርና በምስጋና አንድ ችግኝ እንደተከላችሁልኝ ስሰማ መኖሬ በልዩ መልኩ ትርጉም ሰጥቶኝ ነበር። ሰላምታ ልላክ ብዬ ያደረግኩት ጥቂት ነገር፣ ቁም ነገር ሆኖ ምላሹ አጥለቅልቆኝ እንደነበር ሳስበው እሸማቀቃለሁ። ጸጸትም ተሰምቶኛል።
ሩጫችንን ሮጠዋል። ቀዳዳችንን ደፍነዋል። የበደልናቸውን በሺዎች የሚጠጉ ሴቶች ሳይጠየፉ አቅፈዋል። መድኃኒያለም በቀኙ ይቀፍዎት! ለበደላችን ቅጣት ነበሩ ካትሪንዬ። አንድም ቀን በአካል አይቼዎት ባላውቅም፣ ነፍስዎን ሁሌም አከብራታለሁ።
መልካም ውርስዎ፣ ሥራዎ እንዲቀጥልም ከማንም መንግስታዊ ተቋም በላቀ ሁኔታ ሆስፒታሉን መሰረት አስይዘውታልና ሁሌም ስንዘክርዎ ስናመሰግንዎ እንኖራለን።
Rest in power! 💪
I'l always love you የእኔ እናት ❤
I wouldn't dare to call you 'friend of Ethiopia', as you were indeed 'mother of Ethiopia'.
🙏
/ዮሐንስ ሞላ/