አሁን እንደአገር የእባቡ ታሪክ ላይ ነን!
(አሌክስ አብርሃም)
ፖለቲከኞች ለስብሰባ በተቀመጡበት አንድ ክፍል ውስጥ ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ኮብራ እባብ መሃላቸው ተከሰተ … በሩ ክፍት ነው መስኮቱ ክፍት ነው …በር ላይም የፖለቲከኞቹ ጠባቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው ቁመዋል ….ይሁንና ፖለቲከኞቹ ባገኙት ቀዳዳ ከማምለጥ አልያም ጠባቂዎቻቸውን ድረሱልን ከማለትና ህዝባቸውንም ከማዳን ይልቅ በተራቀቀ ቃልና ሎጅክ …እባቡ ወደክፍሉ በየት በኩል ገባ እና የእባቡ ዝርያና ባህሪ ምንድነው የሚል ክርክር ውስጥ ገቡ … የገባው በመስኮት ሊሆን አይችልም እንደምታዩት መስኮቱ ከፍ ያለና ግድግዳውም ለእባብ የማይመች ነው …በበር ሊሆን አይቸልም … የሆኑ ተቃዋሚዎቻችን ቀድመው አስገብተውት ነው …. እያሉ ሲነታረኩ ….(ለተረት ጊዜ የለንም እንጅ እጨርሰው ነበር)
ጓዶች ! ያለንበት ሁኔታ ይሄን ይመስላል….ኮሮና ቫይረስ ሰው ሰራሽም ይሁን የተፈጥሮ ጣጣ ... በየትም ይግባ በየት አገራችን ውስጥ ገብቷል !! እኛስ … በዚህ ሴኮንዶች እንኳን በሰው ህይዎት ላይ በሚወስኑበት አንገብጋቢ ሰዓት አንዳንዱ ‹‹ ስለአሜሪካና ቻይና የባይሎጅካል ዋርፌር ስለአለም አቀፉ የፖለቲካ የበላይነት መላ ምት ይደረድራል … ሌላው የአሜሪካን ደካማነትና የመሪዋን ‹ቀሽምነት› እንዲሁም በቅርቡ ከፍ ያለ ውድቀት እንደሚጠብቃት ያትታል …ያስጠነቅቃል! አንዳንዱ መላውን አለም ተችቸ ልሙት ይላል !
ጓዶች መጀመሪያ ((((ባገኘነው ቀዳዳ ለመትረፍ በሚረዳን መንገድ ሁሉ ከዚህ ከተጋረጠብን አደጋ እናምልጥ! )))) ከዛ ለቀጣዮቹ መቶ አመታት ሳይንሳዊ ትንታኔ እንሰጣለን ፣ የቻይናን ህዝቦች ከፈለግን ‹እያንዳንዳቸውን በስም እየጠቀስን › እናማቸዋለን …አሜሪካን በደንብ ቡና እየጠጣን እናብጠለጥላታለን ! አሁን እጃችንን እዛጋ ከመጠቆም ሰብሰብ አድርገን እዚህ ጋ እንታጠበው ! ከአምሳ ሚሊየን በላይ ሽንት ቤት እንኳን የሌለው ህዝብ ይዘን …ሃያ ሚሊየን እንደአመትባል በያመቱ ርሃብ የሚያከብር ህዝብ ልጆች ሁነን …ሳሙና እንደጥሎሽ የሚሰጥበት ጭው ያለ ገጠር የሚኖር ህዝብ ያለን ህዝቦች ሁነን ፣ በየመቶ ሜትሩ ከምኝታ ቤቶቻችን የሚፀዳ መፀዳጃ ቤት ያላቸውን ህዝቦች ለማናናቅ ስንጠራራ ፣ እንኳን ደካማ መሪ ወንበሩ ላይ ሬሳም ቢያስቀምጡ ወድቀው የማይወድቁ የተሰራች አገር ባለቤቶችን የኢኮኖሚ ትንታኔ ካልሰጠንባቸው እያልን ስንቀበጣጥር ጊዚያችን እየተበላ ነው ….
በዚች ቅፅበት ለአገራችን ህዝብ የማምለጫ መንገዱ ከአፈትላኪ ዜናና መላ ምት ከምትገኝ እውቀት ተነስቶ አሜሪካን ሙልጭ አድረጎ መሳደብ ሳይሆን ‹‹እጅን በሳሙና ሙልጭ አድርጎ መታጠብ ነው››