ዘመን የየራሷ የውትድርና መልክ አላት! በፊት ሰው ለማዳን "ክተት ሰራዊት" ተብሎ ተጠርቶ፣ ሞቶ አድኖናል። ዛሬ ሰው ለማዳን "ግባ ሰራዊት" ተብሎ ተነግሯል። የሚችል፣ ቤት ገብቶ፣ የሚሰጠውን ምክር ተቀብሎ ሰው ያድናል። ይሄ የእኛ አድዋ ነው። ጦር ሜዳችን ቤታችን ነው። የጦር መሳሪያችን እጃችን ነው።
በእውነቱ ራሳችንን ብንገዛ የምንችለውን ነገር ነው የተጠየቅነውና እንታገል! ግድ ካልሆነብን ከቤት አንውጣ። ከወጣን በምንችለው ሁሉ ተጠንቅቀን እንዋል! አናምሽ፣ አናጭስ። ቤት ስንገባም በቻልነው ልክ ከሰው ጋር አንጠባበቅ! አንተዛዘል! ወደፊት ብዙ እንድንተዛዘል፣ ዛሬን እንሰብስብ!
ይህ ጊዜ ማለፉ አይቀርም። ብዙ ሳይጎዳን ይለፍልን።