ምድራችን ታተኩሳለች። አለም እያሳላት ነው። ታስነጥሳለች።
በተፈጥሯዊ መንገድ ራሷን እያፀዳች ይመስላል። የሰዎች ግርግር ያለልክ መረገጥን በላይዋ መዝለልንና በቃኝ ያለች ይመስላል። ረፍት እየወሰደች ይመስላል ። ዝናብ እንደመታው ፀጉራም ውሻ ከላይዋ ላይ እያራገፈችን ነው፡፡ ግዙፋኑ በአይን በማይታይ ደቂቅ ተረቱ፡፡ ልእለ ኃያላኑ ሌላ ኃይለኛ መጥቶባቸዋል።
ሁሉም በቤቱ ታሽጓል፡፡ ምድሪቱ ብቻዋን ልትቀር ፈልጋች።ግዙፉን ፒራሚድ የገነቡ … የማናይናወጥ ግንብ ያቆሙ … ተአምራትን በምድር የሰሩ የሰው ልጆች ተሸነፉ፡፡ የቬነስ ፏፏቴዎች ብቻቸውን እየጮሁ ነው። ሃይፍል ታወር ራቁቱን ተገትሯል። ታጅመሃል በጎብኚ ማጣት ያዛጋል፡፡ ሰው አንደ ጉንዳን ይተራመስባቸው የነበሩ ታላላቅ ሜትሮፓሊታን ከተሞች ጭርታቸው ያስፈራል፡፡ በዚህ ሳቢያ ውሃዎች ንፁህ ሆነዋል ። የአየር ብክለት እየፀዳ ነው፡፡
እከሌ አምርታው ለእከሌ ያቀበለችው ባዮሎጂካል የጦር መሳሪያ ይሆን እያሉ መላ ይመታሉ? ማነው ነፍሳችንን አሲዞ ቁማር እየተጫወተብን ያለው? የራሺያ ሚሳኤል ፡ የፈረንሳይ ሙዚቃ ፡ የብራዚል ዳንስ ፤ የእንግሊዝ ስነፅሁፍ የአረብ ነዳጅ የአማዞን ጫካ የአፍሪካ አልማዝ አያስመልጥም ። ሰው እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው።
ምድራችን ታተኩሳለች። አለም እያሳላት ነው። ታስነጥሳለች።
መሸሸጊያ ጥግ ሲጠፋ። እዩኝ እዩኝ ያሉ ሁሉ ደብቁኝ ደብቁኝ ሲያመጡ፡፡ ያኔ ሰው ሁሉ እኩል ነው። ቫይረሱ ከሆሊውድ የእውቅና እና የሀብት አምባ እስከ ቤተመንግስት ባለስልጣናትን ደጅ አንኳኩቷል። ታዋቂ ነሽ አዋቂ አልማረም፡፡ ይሆናል ብለን ያልጠበቅነው ሁሉ እየሆነ ነው። ስፖርተኞች ሲፈነጩባቸው የነበሩ ስታዲየሞች ወደ ሆስፒታልነት እየተቀየሩ ነው። ለተጫዋቾችና አሰልጣኞቻቸውም አልራራም ።
ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪና የማይገመት የሆነ ይመስላል። በቀላሉ ከአህጉር አህጉር ዘለለ። የሟቾች እና የተጠቂዎች ቁጥሮች በአለም ዙሪያ በየሰአቱ ያሻቅባል፡፡ በርካታ መሰናዶዎች ተሰርዘዋል ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝመዋል፡፡ የኢኮኖሚ መንኮታኮቱ አያድርስ ነው። እንደ ግሰብ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አለም … ብንተርፍ እንኳ ለማገገም ዳግም ለመቆም ብዙ ዋጋ እንለፋለን፡፡
ምድራችን ታተኩሳለች። አለም እያሳላት ነው። ታስነጥሳለች።
እኔ ለምሳሌ በዘመኔ ወረርሽኝ አያለሁ ብዬ ገምቼም አላውቅም። ህዝቤ ደግሞ የነገሩ ክብደት የገባው አይመስልም ። ኑሮው እንደነበረ ቀጥሏል፡፡
አዲስ እንደመሆኑ መረጃዎቹ ያምታታሉ ምልክቶቹ … መተላለፊያ መንገዶቹ … የአዋቂዎችና የህፃናት የተጋላጭነት ደረጃ ፤ ሙቀት ይቋቋማል አይቋቋም ፤ አየር ላይ ብረት ላይ ልብስ ላይ የሚቀመጥባቸው ሰአታት… ትኩስ ነገር ቀዝቃዛ ነገር … ። ታጠቡ አትሸፈኑ። ተሸፈኑ ታጠቡ። እንሰሳትን ይይዛል?
ጤንነት እንደቀደመው ጊዜ በዘፈቀደ አኗኗር የሚገኝ ነገር አልሆነም፡፡ ራስን መጠበቅ፡፡ አዎ ራስ ጠባቂ ያስፈልገዋል፡፡ የጤናን ነገር ችላ አለማለት። ጤናማ አመጋገብ፡ በቂ እንቅልፍ። ብዙ ውሃ። አካላዊ እንቅስቃሴ ለራስ ጥበቃ ዘብ ናቸው…፡፡
በቀጣዮቹ ቀናት የከፋ ነገር ከሰማንም (ከነገሩን) ወገባችንን ጠበቅ ማድረግ ነው፡፡
አጣዳፊ አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠመን ደጁ ባይናፍቀን። ከምንም ከምንም መገለል፡፡ ራስን ማግለል ፡፡ መሸሸግ፡፡ ከሰው መንጋ መገለል፡፡ ከራስ ጋር ንግግር፡፡ ራስን ማዳመጥ … ይህ አቶ ‘’ራስ’’ እንዴት ጥሩ ሰው መሰላችሁ ?
~ Tsigereda Gonfa