እግዚአብሔርማ አወቀልንና ጊዜ ሰጠን። እኛ ግን አላገጥን።
ሊያነቃን መረጃ የሚሰጡ ሰጠን። እኛ ግን መተኛት ፈለግን።
በአቅማችን ልክ ሊያሽክመን ጠበቀ። እኛ ግን ተወጣጠርን።
በድንቁርና ፍቅር ነደድን። በግድየለሽነት እሳት ተቀጣጠልን።
"የፌስቡክ በሽታ ነው" አሉ፣ እንደኖህ ዘመን ሰዎች ተራቀቅን።
የእኛ ጠባቂ አለ ይጠብቀናል አቦ...ጊዜ አለን" ብለን ቀለድን።
እንግዲያውስ እንንሳ! ለእዬዬም ማያመች ጊዜ እየገሰገሰ ነው
ዛሬ ራሳችንን እንጠብቅ ስለው ለሳቀብኝ እና ለተሳለቀብኝ ወዮ!
ነገ እሱን አያድርገኝ
ነገ እኔን/እኛን አያድርገው
በግብዝነቱ ደጃፍ አያሳልፈኝ
የሙሾ ግጥሙን ይዞ ሲመጣ አያሳየኝ!
😌
~ yohanes
ሊያነቃን መረጃ የሚሰጡ ሰጠን። እኛ ግን መተኛት ፈለግን።
በአቅማችን ልክ ሊያሽክመን ጠበቀ። እኛ ግን ተወጣጠርን።
በድንቁርና ፍቅር ነደድን። በግድየለሽነት እሳት ተቀጣጠልን።
"የፌስቡክ በሽታ ነው" አሉ፣ እንደኖህ ዘመን ሰዎች ተራቀቅን።
የእኛ ጠባቂ አለ ይጠብቀናል አቦ...ጊዜ አለን" ብለን ቀለድን።
እንግዲያውስ እንንሳ! ለእዬዬም ማያመች ጊዜ እየገሰገሰ ነው
ዛሬ ራሳችንን እንጠብቅ ስለው ለሳቀብኝ እና ለተሳለቀብኝ ወዮ!
ነገ እሱን አያድርገኝ
ነገ እኔን/እኛን አያድርገው
በግብዝነቱ ደጃፍ አያሳልፈኝ
የሙሾ ግጥሙን ይዞ ሲመጣ አያሳየኝ!
😌
~ yohanes