የኮሮና ቫይረስ መርከብ ውስጥ ባለ ቦታ ላይ (surface) ለ17 ቀናት መቆየቱን CDC ተናግሯል። ያው ቫይረሱ አዲስ ስለሆነ፣ ጠባዩንም እየቀያየረ ስለሚሄድ፣ እየተኖረ የሚጠና ነው። እኛም እያጠኑ የሚነግሩንን እየሰማን ለመተግበር ትግላችችንን መቀጠል ነው። ያወቅነውንም ትክክለኛ መረጃ ብቻ፣ ለሌሎች ማሳወቅ ነው።
ስለዚህ፥ ቤታችን ውስጥ ወይም ስራ ቦታ ያሉ አዋራ ያለባቸውን፣ እንዲሁም በብዛት ሰዎች የሚነኳቸውን ነገሮች (ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ስልኮቻችን፣ ፕሪንተር፣ የበር እና የቁም ሳጥን እጀታዎች፣ የበር መቃኖች፣ መስታወቶች ወዘተ) በየቀኑ፥ ጸረ ተዋህስያን ማጽጃ ፈሳሽ ተጠቅመን፣ በደንብ ማጽዳት ይኖርብናል።
ለጽዳት የተዘጋጀ ማጽጃ ፈሳሽ (disinfectant) ከሌለን፥ በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 4 የሻይ ማንኪያ በረኪና በመቀላቀል ቤት ውስጥ ማዘጀት እንችላለን። ካጸዳን በኋላ ህጻናት እንዳያገኙት አርቀን እናስቀምጠው።
አትክልት እና ፍራፍሬ በሽታ የመከላከል ጥቅም እንዳላቸው ይጠቀሳል። ብዙ ሰዎችም አትክልት እና ፍራፍሬ ብሉ ብለው ሲመክሩ ነበር። መመገቡ ጥሩ ነው። ነገር ግን፣ እኛ ጋ እስኪደርስ ድረስ ሰው በእጅ ስለሚቀባበላቸው፣ ሎሚን ጨምሮ የትኛውንም ፍራፍሬ ወይ አትክልት ስንመገብ፣ በጸረ ተዋህስያን በደንብ አጥበን መሆን አለበት።
በአጠቃላይ ያልበሰሉ ምግቦችን በመመገብ የሚኖረውን የመበከል ስጋትም፣ ማስወገድ ይገባል። አንድ ጽሁፍ ላይ እንዳየሁት ጥሬ ስጋ እንዳይበሉ ይመከራል። ከዚህ ቀደም ዝም ብለን ተጠቅመን ከነበረ መጨነቅ አያስፈልግም። ለከእንግዲህው በምንችለው መልኩ መጠንቀቅ እው። (እርግጠኛ ባልሆንም፣ ግላጭ ንክኪ ስለሚኖረው ስሜት ይሰጣል)
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን፥ መደበኛዎቹ ጥንቃቄዎች ሊለዩን አይገባም።
1) እጅን በሳሙና በሚታዘዘው መሰረት ለ20 ሰከንድ መታጠብ
2) ባልታጠበ እጅ ፊታችንን አለመንካት
3) ሰዎችን አለመጨበት፣ አለመሳም፤ እንዲሁም ርቀትን ጠብቆ መቆም።
4) ስዎች ከሚበዙባቸው ቦታዎች መራቅ። አለመገኘት። ግድ ሆኖ ከተገኙም ርቀትን ጠብቆ መቆም።
5) የህመም ስሜት (ሳል፣ ትኩሳት፣ የመተንፈስ ችግር፥ ከሶስቱ አንዱ ወይም ከዚያ በላይ፤ አንዳንዴ ደግሞ፥ ጣዕም ወይም ሽታ ለመለየት መቸገር፣ የደረት ህመም) ሲሰማን ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች አግልለን፣ 8335 ወይም 952 መደወል። ምልክቶች ሲሰሙን በፍጹም ከቤት መውጣት የለብንም። ሀኪም ቤትም ቢሆን መሄድ የለብንም። ይልቅስ ስልክ እንደውላለን።
6) በምናስልበት ወይ በምናስነጥስበት ጊዜ ክንዳችንን ወይም መሀረብ ወይም ሶፍት መጠቀም
7) የህመም ምልክቶች ካልታዩ ማስክ አለመጠቀም። ማስክ መጠቀሙን ግድ ከፈለግን፣ የሀኪም ቤቱን ማስክ የጤና ባለሞያዎች እንዲረዱን እጥረት እንዳይከሰት፣ የራሳችንን ማስክ በጨርቅ ቤት ውስጥ ማዘጋጀት እንችላለን።
ይኽን ሁሉ እያደረግን ደግሞ፥ በየእምነታችን ጸሎት!
መረጃውን ለሌሎች አጋሩ!