ጥብቅ መልእክት፡ አቅሙ ላለው ሁሉ፥ በተለይ ከአገር ውጪ ላላችሁ ወዳጆች (ሌሎች ሼር በማድረግ አግዙ!)
ጉዳዩ: ከጸጸት ስለ መዳን
እንደምናየው መንግስት ቁጥሩን ባለበት በይዶት፣ የግዱን እየደነገጠ እና ከቅዠቱ እየነቃ አንዳንድ እርምጃዎችን ውስጥ ውስጡንም ውጭ ውጩንም እየወሰደ ነው። ተወደደም ተጠላን፣ ቆይቶም ሙሉ አገሩን ዘግቶ ወረርሽኙን ከመቆጣጠር ውጭ አማራጭ አይኖረውም። ካልሆነ ግን በሽታ እየተመላለሰ ደቁሶት፣ በዙር በዙር እየተመላለሰ አልቆ፣ ኗሪ አልባ አገር ነው የሚተርፈን።
ስንቀናጣባቸው የነበሩ ነገሮች በሙሉ ዋጋ እያጡ፣ የሰው ልጆችም አቅማቸውን እያወቁ ነው ያሉት። የምንነታረክባቸው አጀንዳዎች ሁሉ፥ ከንቱ እንደሆኑ እየተረዳን ነው። እነሆ እኛ በእውቀት እና ክፋት ልንለያየው ያሰብነውን የዓለም ሕዝብ፣ በሽታ አንድ አድርጎት አንድ ዓይነት ህልም እያየ፣ አንድ አይነት ቅዠት ውስጥ ተነክሮ፣ አንድ አይነት ተአምር እየጠበቀ ነው። ወደ እኛ አገር ሲመጣ ደግሞ ቸልተኝነቱ ለጉድ ነው።
አገር እንዲ በጦርነት ሲታመስ ደግሞ፣ ሁሉም ራሱን እንደመንግስት ቆጥሮ፣ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ማድረግ አለበት። እናም ወገኔ፣ ክፉ ቀን ደጃፍ ላይ አድፍጧልና ነገ እንዳይጸጽተን፣ ዛሬ የእኛ ናት። 3 ሀሳቦች አሉኝ፡
1) ራሳችንን ከመጠበቅ ጎን ለጎን፣ ወደ ቤተሰብ ጎረቤት ዘመድ አዝማድ ደውለን "ለወሬ ነጋሪ እንትረፍ እባካችሁ። የምትባሉትን ስሙ እና የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ። ሁሉም ነገር ስትኖሩ ነው። ይኽ በዓለም የመጣ ነውና፣ ባለመደናገጥ ክፉ ቀንን በጥበብ እናሳልፍ የምንባለውን እንስማ" ብላችሁ በምንችለው ማስፈራሪያ ሁሉ አስፈራርተን፣ ለማሳመን መሞከር ነው። ይሰራል!
ለበዓል "እንኳን አደረሰህ" የምንለው ሰው ጋር፣ ነገ እሱ ወይም ቤተሰቡ ሲሞት ደውለን "አይዞኝ ነፍስ ይማር" ልንለው የምንችለው ጋ ሁሉ እንድረስ። ታናናሾቻችን ላይ እንጩኽባቸው! የምንሰማ ሰዎች እንቆጣ! ቀልዴን አይደለም። ካለዚያ ነገ ይጸጽተናል። "በውዝግብር ኤሰሬ" ይላል ጉራጌ። (አንዴ ከተጸጸቱ ምንም አያደርጉም አይነት ነው። ግን ጉራኛው የልብ ያደርሳል።
2) ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ አገራችን ትውደድም ትጥላም ወደ ሙሉ መዘጋት መሄዷ አይቀርም። የብዙ ሰው ጭንቀት እና አይሰራም የሚልበት ምክንያትም ድህነታችን ነው። እንግዲህ በዚህ ሁሉ ድህነታችን፣ ዓለምን ሁሉ ስራ ያስፈታውን ኮሮና ቫይረስ መቀበል ከቻልን፣ እሱን ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁሉ መቀበላችን አይቀርም። ግን እኛ ሳይረፍድ ምን ማድረግ እንችላለን?
ምንም እንኳን በየአገሩ ሁሉ ኢኮኖሚው ቢመታም፣ ሰው ስራ ፈትቶ ቤቱ ቢውልም፣ ሁሉም ባይሆንም አንዳንዶች ለክፉ ቀን ብለን የያዝናት ጥቂት ገንዘብ አትጠፋምና፣ ለቤተሰቦቻችን በመላክ የሚበሉ ምግቦችን እንዲገዙ እናድርግ። ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን፥ ቤተሰባችን ስላለ ብቻ የሚኖሩ፣ የእኛን እጅ ሊያዩ ለሚችሉ ጎረቤቶች፣ የቻልነውን አድርገን የተወሰነ ምግብ እንዲገዙ ገንዘብ እንላክ። (አንድ ሰው ለቤተሰቡ እና፣ ተጨማሪ ለ2 ወይ ለ3 ቤተሰብ የተወሰነ ነገር ቢያደርግ፣ በየሰፈሩ ጉዳቱ ይቀንሳል)
ከዚያ ባሻገር ግን፥ ነገሩ የምር (serious) እንደሆነ ማንቂያም ጭምር በመሆን ይጠቅማል። ከዚያ ባሻገር ግን፣ ነገ ማድረግ ፈልገን የምንችልበት መንገድ ላይኖር ስለሚችል፣ ዛሬ ሳይረፍድ እናድርገው።
3) መንግስትም ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጥ እና እንደጉዳቱ መጠን ምላሹን አፍጥኖ እንዲሰጥ በምንችለው መልክ እንወትውት። ይሄ የመንግስት ጉዳይ ብቻ አይደለም። የህልውና እና እንደ ሕዝብ የመቀጠል ጉዳይ ነው። ከባድ ጦርነት ነው። በተለይ ከሌሎች አገራት እንቅስቃሴ ጋር ስናየው፣ ያለንበት የድንዛዜ አዘቅት ፍንትው ብሎ ይታየናል።
ሀሳብ ካላችሁ ጨምሩበት!
#Covid19Ethiopia