ታሞ ከመማቀቅ ... ይሉት ተረት ጊዜው አይመስልም።
ማቆ ከማለቅ፤ አስቀድሞ መጠንቀቅ!
አሁን ከተማውን ዞር ዞር ብዬ አይቼው ትንሽ እቃ ሸምቼ ቤቴ ገባሁ።
ብዙዎች አማኞች ነን እያሉ አምላካቸውን የመፈታተን ስራ እየሰሩ ነው የሚመስለው።
ህዝቦች ኮሮና ቫይረስን በተመለከት የምንሰማ የምናየውን ከልብ እንውሰድ።
የሃይማኖት ተቋማት "የመንፈስ ልጆቻችሁን" ገስፁ። የምክር ጊዜው አልፏል።
መንግስት ግለሰቦችና ቡድኖች (አንተን ጨምሮ) ሃላፊነት በጎደለው አኳዃን የሚንቀሳቀሱትን ስለ ሰው ልጅ ህልውና ስትል ተግባርህን በሃላፊነትና በፍትሃዊ መንገድ ተወጣ።
እንኳን ዛሬ፤ በዚህ ዘመን የዛሬ መቶ ዓመትም ቢሆን ኢትዮጽያውያን እያመኑ፤ እሴቶቻቸውን እየጠበቁ አካላዊ መራራቅን ገንዘባቸው በማድረግ ራሳቸውን እንዲጠብቁ፤ በሌላውም ህዝብ ላይ እልቂት እንዳያመጡ ይመክሩ፤ ይመከሩና ይሰሙ ነበር።
የህክምና ጥበባቸው የርቀት ጫፍ ላይ ደርሷል፤ ሃብታቸውም ተዝቆ አያልቅም የተባለላቸው ህዝቦች እንደ ቅጠል እየረገፉ የእኛ መዘናጋት፣ የእኛ መተዛዘል፣ የእኛ የምንችለውን እንኳን ለማድረግ አለመጣር ከእግዜር ጋር ግብግብ የገጠምን ያስመስለናል። የአምላኮቻችንን አይኖች በእንጨት እየወጋን ነው።
ማቆ ከማለቅ፤ አስቀድሞ መጠንቀቅ!
አካላዊ መራራቅ - ላለማለቅ!
ማህበራዊ ቅርርብ - ደካሞችን በጥበብ ለማገዝ!
~ ሱራፌል ወንድሙ