በንግግር መራቀቅ ከንቱ ነው፣ በጥበብ ብዛት መመካትም ከንቱ ነው፣ ከፀሐይ በታችም ምንም አዲስ ነገር የለም! የተቀበልነውን አሻሽለን/አበላሽተን አቀብለን እናልፋለን!
የሰው ልጅ እስከዛሬ ድረስ የሰራው አንዱም ከዚህ ጭንቀቱ አልታደገውም፤ ይኽ ግን የሰው ልጅን ከችግሩ በታች አያደርገውም!
ከችግሩ በላይ ለመሆን የሚችለውን ያህል ይፍጨረጨራል።
የሞት የሽረት ትግል ያደርጋል።
የመጣበትን ጠላት ለመመከት የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም።
በስተመጨረሻም ያሸንፋል።
መድኃኒት፣ ክትባት ያገኛል! ድል አድርጎ ወደ መታበዩ ይሄዳል።
ይሄ ከዚህ በፊት በሰው ልጆች ላይ የድረሱ እና ህልውናውን የተፈታተኑ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ሂደት ነው። በችግር ባትለፈተነበት፣ ፍላጎቱ ባልኖረበት የተፈጠረ መፍትሄ የለም።
በረዶ በሌለበት ስለበረዶ መጥረጊያ መኪና እና ስለቤት ማሞቂያ ማን አስቦ ያውቃል? ሙቀቱ የሰው ልጆችን መተንፈስ እስኪያቅት ድረስ ባልፈተነበት ማን ስለማቀዝቀዣ ተጨንቆ ያውቃል?
እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ከብሩህ አእምሮ ጋር ፈጥሯል። ኑሯቸውን ለማቅለል እየሰሩ፣ የተቀበሉት እያሻሻሉ ቀጥለዋል። ሕይወት ይቀጥላል። እኛ ከዚህ ክስተት ለመማር ምን ያህል ዝግጁዎች ነን? ምን እየተማርንበት ነው?
ይኽም ይታለፋል! እስኪታለፍ ግን ሰለባዎች ላለመሆን፣ መድኃኒት እና ክትባት እስኪገኝ ድረስ ጊዜ ለመግዛት በሚደረገው ጥረት ላይ እንሳተፍ። ጉዳቱን ለመቀነስ እንረባረብ። ራሳችንን እንግዛ፣ የተባልነውን እንተግብር፣ ለሌሎችም ትክክለኛ መረጃዎችን እናካፍል።
#Covid19Ethiopia