✔️ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ለመንግስታት አሳልፎ ሊሰጥ ነው!
-ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ህግን በተከተለ መልኩ ሲጠየቅ ለመንግስት ተቋማት አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታወቀ።ውሳኔው ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ይዞት የነበረውን የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ያለመስጠት ፖሊሲ የሻረ መሆኑ ተገልጿል።
-በዚህም ድርጅቱ ህግን የተከተለ ጥያቄ ሲቀርብለት የተጠቃሚዎቹን አይ ፒ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎችን አግባብ ላላቸው የመንግስት አካላት እንደሚሰጥ አስታውቋል።
-ቴሌግራም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው መስራቹና ዋና ስራ አስፈጻሚው ፓቬል ዱሮቭ ባለፈው ነሐሴ ወር በፈረንሳይ መንግስት መታሰሩን ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል።
-በመተግበሪያው ላይ የሚሰራጩ ፅንፈኛ አቋም ያላቸው ይዘቶችን አልተቆጣጠረም በሚል ክሱ የተመሰረተበት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዋስ ተፈቶ ከአገር እንዳይወጣ መታገዱ ይታወሳል።ውሳኔውን አስመልክቶ ፓቬል ዱሮቭ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ ባሰፈረው መረጃ “የቴሌግራምን ህግ የሚጥሱ ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርና አይፒ አድራሻ ህግን ተከትለው ጥያቄ ላቀረቡ አካላት አሳልፈን እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገናል” ብለዋል።
══════❁✿❁═══════ https://t.me/ethiotipsevery