✅ ኢትዮጵያ በግዛቷ የሚያልፉ ሳተላይቶችን መረጃ መቀበል የሚያስችል ቴክኖሎጂ መግጠሟን ገለጸች።
📌ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት ETRSS1 የተሰኘች ሳተላይት በቻይና አጋዥነት ወደ ህዋ ማምጠቋ ይታወሳል፡፡
📌ይህች ሳተላይት በቻይና እንድትመጥቅ ቢደረግም እንጦጦ በሚገኘው ማዕከል በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቁጥጥር ሲደረግባት መቆየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሺያል ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
📌ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ አያያዝን ጨምሮ የከርሰ ምድር ውሃ መጠንን ለማወቅ፣ የመሬት ላይ ሽፋን እና ለተለያዩ ጥናትና እና ምርምር ስራዎች የሚያግዙ ምስላዊ መረጃዎችን ከዚች ሳተላይት ማግኘቷ ተገልጿል፡፡
📌ኢትዮጵያ በግዛቷ በሚያልፉ ዓለም አቀፍ ሳተላይቶች መረጃዎችን መቀበል እና ተጨማሪ ገቢ ማስገኘት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገጠማን እያካሄደች መሆኑን አስታውቃለች ።
📌የመረጃ መቀበያ ማዕከሉ ከዚህ በፊት የተገነባ ሲሆን አሁን እየተከናወነ ያለው ስራ ከሌሎች ሳተላይቶች መረጃ መቀበል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገጠማ ስራዎችን ማጠናቀቅ መሆኑንም ታውቅዋል ።
📌ይህ ተግባር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚያልፉ የሌላ ሀገራት እና ተቋማት ንብረት የሆኑ ሳተላይቶች በደቂቃ ተሰልቶ የሚገኝ ገቢ ሲሆን ከሳተላይቶቹ ባለቤቶች ጋር በመተባበር እና መረጃዎችን በመቀበል አገልግሎቱን ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ተቋማት በክፍያ ለመስጠት መታቀዱን ሰምተናል፡፡
📌በእንጦጦ ሳተላይት መቆጣጠሪያ ማዕከል የተገነባው ይህ መረጃ መቀበያ ማዕከል ምስሎችን በ7 ነጥብ 3 ዲያሜትር ርቀት ላይ በማንሳት ጥራት ያላቸውን መረጃዎች ለመንግስት ተቋማት በነጻ ለግል ተቋማት ደግሞ በክፍያ እያገኙ መሆኑንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡
══════❁✿❁═══════