Репост из: Isaiah 48 Apologetics
🚩 የዕንባቆም 1:12 ዕብራይስጥና አብዱሉ
በዕን 1:12 ላይ እግዚአብሔር ከዘላለም ጀምሮ እንደነበርና፥ ሰዎቹም እንደማይሞቱ ነብዩ ሲገልጽል እንመለከታለን። የክፍሉ ቀጥተኛና ተፈጥሯዊ ንባብ ይህ ነው። ነገር ግን አንድ ታዋቂ የሙስሊም ዓቃቢ-እምነት ነኝ ባይ ዕን 1:12 አንሞትም ሳይሆን አትሞትም ማለት ነው ብሎ ለመተርጎም ዳድቶታል፦
"አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ #አንሞትም፤ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል" (ዕንባቆም 1:12)
הלוא אתה מקדם יהוה אלהי קדשי #לא_נמות יהוה למשפט שמתו וצור להוכיח (Hab 1:12)
ይህ አብዱል ዕን 1:12 የተረጎመበት መንገድ ፍጹም ብሉይ ኪዳን ለተጻፈበት የዕብራይስጥ ቋንቋ ባዕድና እንግዳ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ዕን 1:12 የአማርኛውና የኢንግሊዘኛው ትርጉሞች እንዳስቀመጡት "አንሞትም" ወይም "we shall not die" ተብሎ ሳይሆን "አትሞትም" ወይንም "you shall not die" ተብሎ ነው መተርጎም ያለበት ብሏል። ይህ እጅግ የአላዋቂዎች ስህተት ነው።
▶️ በመጀመሪያ ደረጃ በዕን 1:12 ላይ "לא נמות/ሎ ናሙት" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ "እንዳንሞት" ተብሎ ተተርጉሟል፦
"እንዲህም አለ። እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፥ እንድንድንና #እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን" (ዘፍ 42:2)
ויאמר הנה שמעתי כי יש־שבר במצרים רדו־שמה ושברו־לנו משם ונחיה #ולא_נמות (Gen 42:2)
በዚህ ስፍራ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ እንዳይሞቱ ምግብ እንዲገዙ ወደ ግብፅ ሲልካቸው እናነባለን። ሲልካቸው "እንዳንሞት" ሲል የተጠቀመው የዕብራይስጥ ሀረግ "לא נמות/ሎ ናሙት" የሚለው ሲሆን በዕን 1:12 ላይ ያለው ራሱ ሀረግ ነው። ትርጉሙም እንዳንሞት እንጂ እንዳትሞት ማለት አይደለም። የብዙ አካላትን አለመሞት የሚጠቁም ሀረግ እንጂ የነጠላ አካልን አለመሞት የሚያመለክት ሀረግ አይደለም። አብዱሉ ይህ ሀረግ የነጠላ አካልን አለመሞት ያሳያል ማለቱ የቋንቋውን አላዋቂነት ያሳያል
✏️ በዕብራይስጥ ቋንቋ "እንሞታለን" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "נמות/ናሙት" ሲሆን በድርብ ግስ ተናጋሪው ራሱን ከሌሎች አካላት ጋር በመጨመር እርሱም እነዚያም አካላት እንደሚሞቱ ለመግለጽ ወይንም ደግሞ ከአንድ በላይ አካላት ራሳቸውን አስመልክቶ እንደሚሞቱ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው።
ለምሳሌ፦
"እነሆም፥ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፤ እናንተ። ነገ #እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል" (ኢሳ 22:13)
והנה ששון ושמחה הרג בקר ושחט צאן אכל בשר ושתות יין אכול ושתו כי מחר #נמות (Is 22:13)
በዚህ ስፍራ ላይ በኢየሩሳሌም ያሉ ሰዎች እንደሚሞቱ መናገራቸውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጥ ቃል "נמות/ናሙት" የሚለው ቃል ነው። ስለዚህ ይህ ቃል ብዙ አካላት እንደሚሞቱ ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው ማለት ነው።
ሌላ ምሳሌ፦
"አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን #እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን" (ዘዳ 5:25)
ועתה למה #נמות כי תאכלנו האש הגדלה הזאת אם־יספים אנחנו לשמע את־קול יהוה אלהינו עוד ומתנו (Deut 5:25)
በዚሁ ቦታም እንዲሁ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔር ድምፅ እየሰሙ ከቀጠሉ እንሞታለን ማለታቸውን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ይኸው "נמות/ናሙት" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው። ስለዚህ ይህ ቃል ብዙ አካላት እንደሚሞቱ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ለመሆኑ ይህ ሌላኛው ማሳያ ነው።
♦️ ብዙ አካላት እንደሚሞቱ የሚገልጸው የዕብራይስጥ ቃል ይህ ሲሆን፥ ከዚህ በተቃራኒው አለመሞታቸውን ለመግለጽ ከዚህ "נמות/ናሙት" ከሚለው ቃል ፊት ለፊት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊቱ እንደ prefix ይገባል። "לא/ሎ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "not" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (Strong's H3808) ተቃራኒነትን፥ የአንድ ነገር አለመሆንን ለማመልከት ከግሶች በፊት ይገባል።
ለምሳሌ፦
"ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው። እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው፥ እኛም ተነሥተን #እንሄዳለን" (ዘፍ 43:8)
ויאמר יהודה אל־ישראל אביו שלחה הנער אתי ונקומה #ונלכה ונחיה ולא נמות גם־אנחנו גם־אתה גם־טפנו (Gen 43:8)
በዚህ ስፍራ ላይ ይሁዳ ከቢንያም ጋር እንደሚሄዱ ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "נלכה/ንላኻ" የሚለው ቃል ነው። ከአንድ በላይ አካላት እንደሚሄዱ ከሚገልጹት የዕብራይስጥ ቃላት አንዱ ይህ ቃል ነው
✍️ ይኸው ራሱ የዕብራይስጥ ቃል አለመሄድን እንዲያመለክት ሲፈለግ ግን "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ይገባል፦
"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን። #አንሄድባትም አሉ" (ኤር 6:16)
כה אמר יהוה עמדו על־דרכים וראו ושאלו לנתבות עולם אי־זה דרך הטוב ולכו־בה ומצאו מרגוע לנפשכם ויאמרו #לא_נלך (Jer 6:16)
በዚህ ስፍራ ላይ በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበሩ አይሁድ በቅኑ መንገድ ላይ አንሄድም ማለታቸው ተገልጾ እንመለከታለን። በዚህ ስፍራ ላይ አለመሄዳቸው የተገለጸው በዘፍ 43:8 ላይ ያለው "נלכה/ንላኻ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ገብቶ ነው። ስለዚህ እንደማይሄዱ ለማመልከት እንሄዳለን ከሚለው ቃል ፊት ለፊት ያ ቃል እንደ prefix ገብቷል። ይህ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ሲገባ ተቃራኒነትን፥ ያ ነገር አለመሆኑን እንደሚገልጽ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው።
ሌላ ምሳሌ፦
"ሕዝቡም። ምን #እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ" (ዘጽ 15:24)
וילנו העם על משה לאמר מה #נשתה (Ex 15:24)
በዚህ ቦታ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ምን እንጠጣለን ብለው ሲያንጎራጉሩበት እንመለከታለን። መጠጣታቸውን የሚገልጸው የዕብራይስጥ ቃል "נשתה/ናሽታህ" የሚለው ቃል ነው። ከአንድ በላይ አካላት እንደሚጠጡ የሚገለጽ የዕብራይስጥ ቃል ነው
✍️ ይኸው ራሱ የዕብራይስጥ ቃል አለመጠጣትን እንዲያመለክት ሲፈለግ ግን "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ይገባል፦
"21-22 እስራኤልም። በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጕድጓድም ውኃን #አንጠጣም፤ ከምድርህ ዳርቻ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን ብለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላኩ" (ዘኍ 21:21-22)
אעברה בארצך לא נטה בשדה ובכרם #לא_נשתה מי באר בדרך המלך נלך עד אשר נעבר גבלך (Num 21:21-22)