✍🏽ሕያው
በገመድ ላይ የሚራመድ..
ባለጉዞ..
ይወጥናል መራመጃ ከድር ሰበዝ አንድ መዞ.
ይሟገታል ንቁ አ'ምሮ
ድር እንዳይዘልቅ ጥንቱ ያውቃል.
አስር ቢገልጥ አንዱ አያምንም
ከመዝገቡ አቅመኛ ቃል.
ንቀስ ቢባል መዛግብቱን
ለእውነቱ ማስረገጫ.
ከጥራዙ ምዕራፍ ላይ
ስለተጓዥ መንገድ መውጫ.
እንዲህ ይላል..
በብርሀን ምንጣፍ መሀል
ማን ሊያይ ቻለ የድር ንጣት.
የእግርን ሸክም አትችለውም
ንፋሱ ነው የሚንጣት.
ድር ያመነ..
አልደረሰም ከወጠነው.
ቃላችንን..
ከምናየው ገነባነው.
እውነቱ ልክ ሰውነትን ያልዘነጋ.
ራስ ሚዛን ብርሀን ሳያይ የማይነጋ.
ድር ያመነ ቃል ይፅፋል..
ሸረሪቷ ገመድ ገምዳ ቤት ሰድራ ልጅ ወለደች.
ሸማኔዋ ጋቢ ሰርታ ለጎጆዋ ብርድ አገደች.
ሰው ምንድነው?..
በገመድ ላይ የሚራመድ..
ባለጉዞ..
ይወጥናል መራመጃ ከድር ሰበዝ አንድ መዞ.
ይሟገታል ንቁ አ'ምሮ
ድር እንዳይዘልቅ ጥንቱ ያውቃል.
አስር ቢገልጥ አንዱ አያምንም
ከመዝገቡ አቅመኛ ቃል.
ንቀስ ቢባል መዛግብቱን
ለእውነቱ ማስረገጫ.
ከጥራዙ ምዕራፍ ላይ
ስለተጓዥ መንገድ መውጫ.
እንዲህ ይላል..
በብርሀን ምንጣፍ መሀል
ማን ሊያይ ቻለ የድር ንጣት.
የእግርን ሸክም አትችለውም
ንፋሱ ነው የሚንጣት.
ድር ያመነ..
አልደረሰም ከወጠነው.
ቃላችንን..
ከምናየው ገነባነው.
እውነቱ ልክ ሰውነትን ያልዘነጋ.
ራስ ሚዛን ብርሀን ሳያይ የማይነጋ.
ድር ያመነ ቃል ይፅፋል..
ሸረሪቷ ገመድ ገምዳ ቤት ሰድራ ልጅ ወለደች.
ሸማኔዋ ጋቢ ሰርታ ለጎጆዋ ብርድ አገደች.
ሰው ምንድነው?..