ብቻ አልሙት🤭
በፋኢዛ ✍
ብቻ እኔ አልሙት....እኔ አልሙት እንጂ......ከሞትኩ ተአምር ይፈጠራል ....ድንቅ ተዐምር .....አዎ እኔ አልሙት እንጂ ከሞትኩ ለሰርጌ ያልወጡ ሺ ብሮች ለሰደቃ ይባክናሉ.......ብቻ አልሙት እንጂ የሞቴን ቀን ሲቆጥሩ የነበሩ ባላንጣዎቼ በእምባ ታጥበዉ ...በጥቁር ተከፍነዉ እኔን እኔን እያሉ ይመጣሉ..... አልሙት እንጂ ከሞትኩ ክፉ ናት ያሉኝ ሁላ የዋህ ሰዉ አጣን እያሉ ደረታቸዉን ይወግራሉ .......ከምር አልሙት እንጅ አበድሩኝ ቡዬ ፊት የነሱኝ ሁሉ የሬሳ ሳጥን ለመግዛት ያዋጣሉ ....ለሷ ያልሆነ! ይላሉ ......ብቻ አልሙት እንጂ እኔ ከሞትኩ...... ምን አዉቅልሻለሁ! ...ገደል ግቢ! ....አላዉቅልሽም እያለ ያጥላላኝ ተፈቃሪዬ .....ከሀዘን ማቅ ስገባ እንደዋዛ የገፋኝ ተፈቃሪዬ ...በህይወት ሳለሁ እንዲሰጠኝ የለመንኩትን አበባ መቃብሬ ላይ ሊያስቀምጥ ይመጣል ....በህይወት ሳለሁ ያላለኝን አፈር ለሆነዉ ገላዬ ያወራል .............ብቻ እኔ አልሙት እንጂ እነዛ ይቺ እብድ ስታስጠላ! ብለዉ ያሙኝ ሁላ ስኳርና ዳቦ ይዘዉ ወይኔ ጓደኛዬ! እያሉ ይመጣሉ ..... ስኖር ደዉለዉ ያልጠየቁኝ አራስ እያለሁ ሚያዉቁኝ ዘመድ አዝማዶች ሁሉ ....ምነዉ በለጋነቷ! እያሉ ይጓርፋሉ ................ብቻ አልሙት እንጂ ብዙ የአፍቃሪ እንባዎች ብዙ የድራማ እንባዎች ይፈሳሉ ........ለኔ ሳይሆን ለራሳቸዉ ያለቅሳሉ! ምናለ እንዲህ ባደረግንላት ይላሉ......ብመለስምኮ አይቀየሩም! ግን አንደማልመለስ ስለሚያዉቁ እንድመለስ ይፈልጋሉ .....አንዳንዴ ብሞትና አልቃሾቼን አይቼ ብመለስ እላለሁ ......ግን አይሆንም እሞታለሁ! ስሞት ያልነበሩ ነገሮች ይኖራሉ ....ስኖር ያላስታወሱኝ ስሞት ይናፍቁኛል....ስኖር የገፉኝ ሳልኖር ይፈልጉኛል....የአብሮነቴ ትርጉም ይገባቸዋል! ይጎድላሉ! ግን አልኖርም! አልመለስም! ዛሬ ግን አለሁ ስሞት የምትፈጥሩትን ተዐምር ዛሬ መፍጠር አትችሉምን?????????????
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
For any comment
@mornin_bot
❥❥________⚘_______❥❥
Join
@faiza_kiza
@faiza_kiza
Don't forget to Share for your beloved please