በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ
....................................................
መጋቢት 2/2016ዓ.ም (ትሚ) በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 (አንድ መቶ አስራ አራት) ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ በደብዳቤው ተመልክቷል ።
ከየካቲት 6-11/2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119, 145 ተፈታኞች ተፈትነዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ሪፎርሞች አንዱ የሆነው መውጫ ፈተና ተመራቂዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ተገቢውን እውቀትና ክህሎት መቅሰማቸውንና ብቁ መሆናቸውን ዒላማ ያደረገ በመሆኑ ፈተናው በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ ነው።
https://t.me/Ethio_Education_24
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻 ቻናል👇
https://t.me/Ethio_Education_24_news