George soros (1930 - Now)
ጆርጅ ሶሮስ (በትክክለኛው ስሙ György Schwartz) በ1930 ዓ.ም በሀንጋሪ (Hungary) ከአይሁድ ቤተሰብ ተወለደ። በ1944 ዓ.ም ናዚዎች ሀንጋሪን በወረሩ ጊዜ እሱ እና ቤተሰቡ ሸሽተው ለቀዋል::
በ17 ዓመቱ ወደ እንግሊዝ ሄዶ በለንደን(London) የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት (LSE) ፍልስፍናን አጠናቀቀ። በዚያን ጊዜ የካርል ፖፐር (Karl Popper) የ Open Society ፅንሰ-ሀሳብ ተምሯል::
በ1956 ዓ.ም ወደ ኒውዮርክ ሄዶ በፋይናንስ ዘርፍ ሥራ ጀመረ። ሶሮስ በ1969 የራሱን የኢንቨስትመንት ፈንድ (Quantum Fund) መሰረ::
ሶሮስ በ1992 ዓ.ም የእንግሊዝ ፓውንድ ስተርሊንግ (GBP) ከአውሮፓዊ የምንዛሪ አውታር (ERM) እንደሚወድቅ በመገመት 1 ቢሊዮን ዶላር በአንድ ቀን በመስራት ታሪክ ፈጠረ። ከዚያ ጀምሮ "The man who Broke the Bank of England" ተብሎ ተጠራ።
ሶሮስ የፍልስፍናውን ራእይ በመከተል Open Society Foundations መሠረተ። ይህ ድርጅት በዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች እና ትምህርት ላይ በአለም ዙሪያ ቢሊዮኖችን ዶላር ያፈሳል::
በአሁኑ ጊዜ (2025)
በ94 ዓመቱ እያለ፣ ሶሮስ አሁንም በፖለቲካ እና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ተገኝቶ ይገኛል።
@Forex_Trade_433et @Forex_Trade_433et