የኔ ሰው
(ፉአድ ሙና)
.
መቶ ብር ለታክሲ
ሀምሳ ለማስቲካ፣
ካፌ ተሰብስቦ
ሞኝ ሲያውካካ።
መቶ ብር ለጀነት
አለች እጅ አውጥታ፣
ካፌ ትሰጣበት
ጊዜ መች አግኝታ።
መቶ ብር ለጀነት!
አይኗን አውቀዋለሁ
አያይም ደግ እንጂ፣
ጥርሷን አውቀዋለሁ
ነጭ የፍቅር ፈንጂ!
ሰለዋት ተሞልቶ
አይገዳትም ሆዷ፣
የጀነት ስራ ነው
የህይወት መንገዷ!
መቶ ብር ለጀነት!
የታሸገ ውሀ
ብትጠጣም አማርጣ፣
ጭንቀቷ ላጣው ነው
ይህን የሪዝቅ እጣ!
ያብሰለስላታል...
እንቅልፍ ይነሳታል...
የወንድሟ ጥማት
የእህቷ መደፈር፣
በጠብታ ውሀ
የሚስኪኑ መክፈር።
ያማታል ቆንጆዬን
እንቅልፏስ መች መጥቶ፣
ከጀነት ሲጨለፍ
ሰው ደጋፊ አጥቶ።
ያስነባታል በጣም!
መቶ ብር ለጀነት!
ገረፋት የሰው ፊት
ብታደገው ብላ፣
ሺህ ሰው ረገጠው
ያንን ቅዱስ ጥላ።
መቶ ብር ለጀነት
ትላለች የኔ ሰው፣
ኩፖኗን ይዛ ነው
`ምትመላለሰው።
መቶ ብር ለጀነት!
በቆሻሻ ውሀ
በሽታ እየጠጣ፣
ህይወቱ ለሚያልፈው
ህክምና እያጣ!
ያ ረቢ ለሚለው
ገጠር ተቀምጦ፣
እንዳይጫንበት
እንዲያምን መርጦ!
ትሽከረከራለች
ከኩፖኗ ጋራ፣
ወትሮም አንደኛ ናት
ለጀነት ሰው ስራ!
መቶ ብር ለጀነት!
መቶ ብር ለኔ ሰው፣
ፊት እየገረፋት
ኩፖኖቿን ሸጣ ለምትመለሰው!
***
መታሰቢያነቱ
በየገጠሩ የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ኩፖን እየሸጡ የሰው ፊት ለሚገርፋቸው ኢፋድዮች ይሁንልኝ! የኔ ሰው እናንተ ናችሁ!
.
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
መቶ ብር ለታክሲ
ሀምሳ ለማስቲካ፣
ካፌ ተሰብስቦ
ሞኝ ሲያውካካ።
መቶ ብር ለጀነት
አለች እጅ አውጥታ፣
ካፌ ትሰጣበት
ጊዜ መች አግኝታ።
መቶ ብር ለጀነት!
አይኗን አውቀዋለሁ
አያይም ደግ እንጂ፣
ጥርሷን አውቀዋለሁ
ነጭ የፍቅር ፈንጂ!
ሰለዋት ተሞልቶ
አይገዳትም ሆዷ፣
የጀነት ስራ ነው
የህይወት መንገዷ!
መቶ ብር ለጀነት!
የታሸገ ውሀ
ብትጠጣም አማርጣ፣
ጭንቀቷ ላጣው ነው
ይህን የሪዝቅ እጣ!
ያብሰለስላታል...
እንቅልፍ ይነሳታል...
የወንድሟ ጥማት
የእህቷ መደፈር፣
በጠብታ ውሀ
የሚስኪኑ መክፈር።
ያማታል ቆንጆዬን
እንቅልፏስ መች መጥቶ፣
ከጀነት ሲጨለፍ
ሰው ደጋፊ አጥቶ።
ያስነባታል በጣም!
መቶ ብር ለጀነት!
ገረፋት የሰው ፊት
ብታደገው ብላ፣
ሺህ ሰው ረገጠው
ያንን ቅዱስ ጥላ።
መቶ ብር ለጀነት
ትላለች የኔ ሰው፣
ኩፖኗን ይዛ ነው
`ምትመላለሰው።
መቶ ብር ለጀነት!
በቆሻሻ ውሀ
በሽታ እየጠጣ፣
ህይወቱ ለሚያልፈው
ህክምና እያጣ!
ያ ረቢ ለሚለው
ገጠር ተቀምጦ፣
እንዳይጫንበት
እንዲያምን መርጦ!
ትሽከረከራለች
ከኩፖኗ ጋራ፣
ወትሮም አንደኛ ናት
ለጀነት ሰው ስራ!
መቶ ብር ለጀነት!
መቶ ብር ለኔ ሰው፣
ፊት እየገረፋት
ኩፖኖቿን ሸጣ ለምትመለሰው!
***
መታሰቢያነቱ
በየገጠሩ የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ኩፖን እየሸጡ የሰው ፊት ለሚገርፋቸው ኢፋድዮች ይሁንልኝ! የኔ ሰው እናንተ ናችሁ!
.
@Fuadmu