ከመክበር በር ላይ!
(ፉአድ ሙና)
.
ጊዜው በረታ ..... የአይናቸው ማረፊያ ኸዲጃን እና ከለላ አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ቀበሩ። የመካ ሰዎች ነገር ከቀን ወደ ቀን ቢጠናቸው፤ ነብይ በሀገሩ አይከበርምና የሌላ ቀዬ ሰዎች ከተመለሱልኝ ብለው ወደ ጧዒፍ ከዘይድ ኢብኑ ሀሪሳ ጋር ተጓዙ።
ከጧዒፍ ቀዬ ቆሙ .... እኒያ የልቀት ልክ ... ለአይን የሚታፈሩ ነብይ .... ለተላኩበት ጥሪ ሲሉ የጧዒፍ መሪዎችን ተዋደቁ። እናንተ የጧዒፍ ሰዎች ሆይ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ወዲያ በሉና የአላህን አንድነት አውጁ ሲሉ ለፈፉ። የጧዒፍ ሰዎች በእጄ የሚሉ አይነት አልነበሩም። ይልቁንስ የተከበረውን ነብይ እና ዘይድ ኢብኑ ሀሪሳን በድንጋይ ይወግሯቸው ገቡ። ህፃናት እና እብዶቻቸውን አሰማሩባቸው። ከውዱ ነብይ ገላ ደም ፈሰሰ። ጫማቸው በደም ሞላ። ዘይድ በቻለው አቅም ከለላ ሊሆናቸው ይሞክራል። በዚህ መልኩ ከጧዒፍ ከተማ ለቀው ወጡ። ተደብድበው .... ተዋርደው .... ጧዒፍን ለቀቁ።
ከጧዒፍ ወጣ እንዳሉ መልዕክተኛው በተሰበረ ልብ ወደ ጌታቸው ተጣሩ።
«اللهم إليك أشكو ضعف قوتي، وقلة حيلتي، وهواني على الناس، يا أرحم الراحمين، أنت رب المستضعفين، وأنت ربي، اللهم إلى من تكلني؟ إلى بعيد يتجهمني، أم إلى عدو ملكته أمري؟ إن لم يكن بك غضب علي فلا أبالي، غير أن عافيتك أوسع لي، أعوذ بنور وجهك الذي أشرقت به الظلمات، وصلح عليه أمر الدنيا والآخرة، أن ينزل بي سخطك، أو يحل علي غضبك، لك العتبى حتى ترضى ولا حول ولا قوة إلا بالله
አላህ ሆይ! የአቅሜን ደካማነት፣ የዘዴዬን ማነስ፣ በሰዎች ዘንድ መዋረዴን ወደ አንተ አቤት እላለሁ! አንተ የአዛኞች አዛኝ የሆንክ ጌታ ነህ! አንተ የደካማዎች ጌታ ነህ! አንተ ጌታዬ ነህ! አላህ ሆይ ወደማን ታስጠጋኛለህ? ፊቱን ወደሚያጨፈግግብኝ ባዕድ ወይስ በጉዳዬ ላይ ስልጣን ለሰጠኸው ጠላት? አንተ ካልተቆጣህብኝ ግድ የለም። ግን ከአንተ የሆነ ጤንነት እና ደህንነት ለኔ በጣም ሰፊ ነው። የአንተ ቁጣ እንዳይወርድብኝ ጨለማዎች በበሩበትና በሱ ላይ የአዱንያና የአኼራ ጉዳዮች በተበጁበት በፊትህ ብርሀን እጠበቃለሁ። እስከምትወድልኝና እስከምትቀበለኝ ድረስ ስሞታዬን ለአንተ አቀርባለሁ። በአንተ እንጂ ዘዴም ሆነ ኃይል የለም።»
ከዚህ ዱዓ በኋላ የአላህ መልዕክተኛና ባልደረባቸው ወደ መካ ጉዟቸውን ቀጠሉ። መልዓኩ ጂብሪል (ዓሰ) ወደ ነብያችን በመምጣት «ሙሀመድ ሆይ ህዝቦችህ ያሉህን ጌታህ ሰማ፣ ማስተባበላቸውንም አየ! ጌታህ የተራራ መልዓክትን የምታዛቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ወዳንተ ልኳል!» አላቸው።
የእዝነት ተምሳሌቱ ነብይም «ከልጅ ልጆቻቸው እንኳን ቢሆን አላህን በብቸኝነት የሚገዛ ይወጣ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።» ሲሉ የእልቂቱን ደመና አነሱ። ላደማቸው .... ለደበደባቸው .... ላዋረዳቸው ህዝብ ምላሻቸው ይህ ነበር። የአላህ ሰላት እና ሰላም በእዝነተ ሰፊው ነብይ ላይ ይሁን!
ወደ መካ ሲደርሱ በሀገሩ ከለላ የላቸውምና ቁረይሾች እንደሚገድሏቸው ገባቸው። በጃሂሊያ ጊዜ የነበረ ውብ ባህል ነበራቸው። ከለላ መስጠት! የአለሙ ጌጥ ከለላ ይሰጧቸው ዘንድ ሶስት ሰዎች ጋር መልዕክት ላኩ። ሁለቱ አሻፈረኝ ቢሉም ሙጥዒም ኢብኑ አዲይ ጥሪውን መለሰ። ልጆቹን አስታጥቆ ውዱን ነብይ አጅቦ ወደ መካ አስገባ። ነብያችን የበድርን ጦርነት ካሸነፉ በኋላ ይህን ሰው አውስተዋል። «ሙጥዒም በጠየቀኝ ምርኮኛዎችን ሁሉ በፈታሁለት ነበር!» ብለዋል። ነገር ግን ሙጥዒም ከበድር በፊት ወደማይቀርበት ወደ ቀጣዩ አለም ተጉዞ ነበር።
ከጭንቅ በኋላ ብስራት እንዳለ ለዓለም ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ አላህ (ሱወ) በረጀብ በ27ኛው ለሊት የኢስራዕ ወል ሚዕራጅን ድግስ አሰናዳላቸው። ምድር ላይ በሰው ከተዋረዱ በኋላ ሰማይ ላይ ወስዶ አከበራቸው። ቡራቅን ተጭነው «ሀዬ» እያሉ ከጅብሪል ጋር በምድር ወደ መስጂደል አቅሳ ጋለቡ። ቡራቅ የሚሉት ጉድ አይኑ ማየት የሚችለውን ያህል በብርሀን ፍጥነት ይራመድ ነበር። አላህም በኢስራዕ ምዕራፍ ገድሉን ዘከረ።
«سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡»
(ኢስራዕ፣ 1)
ጧዒፍ ላይ በድንጋይ የተደበደቡት ነብይ በተቀደሰው ቤት ነብያትን ኢማም ሆነው አሰገዱ። ከዚያም ሚዕራጅ ተከተለ። ከጅብሪል ጋር ጉዞ ወደ ሰማይ ቤት! በየሰማዩ የተለያዩ ነብያትን እያገኙ ወደ ሲድረተል ሙንተሀ አቀኑ።
«مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَى๏أَفَتُمَارُونَهُ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ๏ وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ๏ عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ๏ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ๏ إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ๏ مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ๏ لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም። ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡»
(ነጅም 11 –18)
በዚህ ጉዞ ሲድረተል ሙንተሀ ላይ ሲደርሱ ጅብሪልን በተፈጠረበት ቅርፅ ተመልክተውታል። ከጌታቸው ጋር አውግተውም ሰላትን እና የላሚቷን ምዕራፍ የመጨረሻ አንቀፆች ተቀብለዋል።
ውዱ ነብይ ወደ ምድር እንደተመለሱ ይህንን ተዓምር ተናገሩ። ሰው ይሳለቅ ገባ። ጭራሽ በአንድ ለሊት ከመካ በይተል መቅዲስ ድረስ ዘለቅኩ፤ ወደ ሰማይም አረግኩ አለ ብለው ተሳለቁ። ይህ ወሬ የአቡበከር ጆሮ ደረሰ። «እርሱ ይህን ብሏል?» ሲሉ ጠየቁ። «አዎን ብሏል!» የሚል ምላሽን አገኙ። «እንግዲያማ ብሎ እንደሆን እውነቱን ነው።» ሲሉ ተቀበሉ። ሲዲቅ የተባለውን ማዕረግ ያስገኛቸው ይህ ነበር። «ከሰማይ መልዕክት ይመጣልኛል ሲለኝ ያመንኩትን ሰው ወደ ሰማይ ሄድኩ ቢለኝ ምን ይገርመኛል።» ሲሉ እምነታቸውን አረጋገጡ።
ከነብዩ የኢስራዕ ወል ሚዕራጅ ጉዞ አንድ ትልቅ ትምህርት እንማራለን። ከችግር በኋላ በእርግጥ ድሎት አለ።
«ምንድን ቢከፋህ
የበደል በትር፣ ቢያሳጣህ አቅም፣
አደራ አስታውስ
ከሚዕራጅ በፊት፣ የጧዒፍ በደል እንደሚቀድም! »
በአለማቱ ጌጥ .... በክብራችን መሰረት .... በእዝነቱ ቁንጮ .... በመወደድ ሚዛን .... በድሀው ነብይ ላይ የጌታው ሰላት እና ሰላም ይውረድ!
.
@Fuadmu