•
•
አድዋ
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
የጥቁሮች ኩራት የሀበሻ ገድሉ
ነጭን ያዋራደ በወርቃማው ድሉ
በአይቀጡ ቅጣት አለም ያስደነቀ
ለጭቁኖች ፋና ብርሃን ያፈለቀ
የእምዬ ዘሮች ነብስን የገበሩ
ደማቸውን ሰጥተው ሀገር ያስከበሩ
እኒያ ባለወኔ ልበ ደፋር ጀግኖች
ታሪክን ሰርተዋል ዛሬ ላሉት ስሞች
ከምስራቅ ፣ ከምዕራብ
ከሰሜን ፣ ከደቡብ
በአንድ የዘመቱ የኢትዮጲያ ልጆች
ሀገር ስትደፈር የነደዱ ልቦች
ድልን ያወረሱ አሁን ላለን ህዝቦች
ምስክር ተራሮች...!
ሶሎዳ ተራራ ሲከተም ለጠላት
የማሪያም ሸዊቶ ቁልቁለት አቀበት
በአዲ ተቡን ግንባር ከፊት ሲዋደቁ
በእግዚሃር አሳየኝ ሱሬ ሲያሶልቁ
ይመስክር ተራራው!
ያንበረከክንበት ነጭን ከነ ጎራው
አወይ የዛን ግዜ አወየው ክተት
እናት ስትነካ ያልተፈራው ሞት
አንገት የሰጡበት ድንበር ላለፉት
በደማቅ ተፅፏል ከታራኮች አውራ
የምኒልክ ጀብዱ የጣይቱ ስራ
የባልቻ አይፈሬነት የሺዎች ፉከራ
ሠራዊት ፈረሱ ሲበር እንዳሞራ
የጋሻውን እምብርት በመሬት ሲያጠቅሰው
ጎራዴውን ባየር ደርሶ እየቀዘፈው
በቆረጠ ቁጣ በሚሳብድ መንፈስ
ወራሪን ከስሩ.........
ደባለቁት ካፈር ሀሞቱ እስኪፈስ
ድል ተጎናፀፉ ዳግማዊ ከበረ
ቀኙን ስለሠጠው ቆሞ በአንድ እግሩ
በእንዳማርያም ላይ..........
ምስጋና አቀረበ ለታላቅ እግዜሩ
አድዋ..... አድዋ..... ጠላት ያፈረበት
የኢትዮጲያዊን ኩራት
ያፍሪካዊያን ኩራት
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
•
አድዋ
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
የጥቁሮች ኩራት የሀበሻ ገድሉ
ነጭን ያዋራደ በወርቃማው ድሉ
በአይቀጡ ቅጣት አለም ያስደነቀ
ለጭቁኖች ፋና ብርሃን ያፈለቀ
የእምዬ ዘሮች ነብስን የገበሩ
ደማቸውን ሰጥተው ሀገር ያስከበሩ
እኒያ ባለወኔ ልበ ደፋር ጀግኖች
ታሪክን ሰርተዋል ዛሬ ላሉት ስሞች
ከምስራቅ ፣ ከምዕራብ
ከሰሜን ፣ ከደቡብ
በአንድ የዘመቱ የኢትዮጲያ ልጆች
ሀገር ስትደፈር የነደዱ ልቦች
ድልን ያወረሱ አሁን ላለን ህዝቦች
ምስክር ተራሮች...!
ሶሎዳ ተራራ ሲከተም ለጠላት
የማሪያም ሸዊቶ ቁልቁለት አቀበት
በአዲ ተቡን ግንባር ከፊት ሲዋደቁ
በእግዚሃር አሳየኝ ሱሬ ሲያሶልቁ
ይመስክር ተራራው!
ያንበረከክንበት ነጭን ከነ ጎራው
አወይ የዛን ግዜ አወየው ክተት
እናት ስትነካ ያልተፈራው ሞት
አንገት የሰጡበት ድንበር ላለፉት
በደማቅ ተፅፏል ከታራኮች አውራ
የምኒልክ ጀብዱ የጣይቱ ስራ
የባልቻ አይፈሬነት የሺዎች ፉከራ
ሠራዊት ፈረሱ ሲበር እንዳሞራ
የጋሻውን እምብርት በመሬት ሲያጠቅሰው
ጎራዴውን ባየር ደርሶ እየቀዘፈው
በቆረጠ ቁጣ በሚሳብድ መንፈስ
ወራሪን ከስሩ.........
ደባለቁት ካፈር ሀሞቱ እስኪፈስ
ድል ተጎናፀፉ ዳግማዊ ከበረ
ቀኙን ስለሠጠው ቆሞ በአንድ እግሩ
በእንዳማርያም ላይ..........
ምስጋና አቀረበ ለታላቅ እግዜሩ
አድዋ..... አድዋ..... ጠላት ያፈረበት
የኢትዮጲያዊን ኩራት
ያፍሪካዊያን ኩራት
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel