መስዕዋት አንዴ ብቻ
ዕብራውያን 10 ፡26፤ የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥
የአድስ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዐት ከብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዐት ጋር ቡብዙ ይለያያል ።
የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት የምደረገው አንድ ሰው ሀጢአኛ እንደ ሆነ ስሰማው የኮርማንና የዋኖስን እንድሁም ለሎችን ለመስዋዕትነት የሚሆኑትን እንስሳት ሀጢአትን በሰራበት ሰዓት ሁሉ ያቀርባል ። ይህ የመሥዋዕት ዑደት እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ድረስ የቀጠለ የመሥዋዕት ሥርዓት ነበር።
በዚህ ሥርአት መሥዋዕትነት ይደገማል ሀጢአት ሲደገም አሁንም አሁንም መሥዋዕቱን ይደጋግሙታል።
ነገር ግን አዲስ ኪዳን ማለትም ኢየሱስ በደሙ አዲሱን ሥርዐት ከጻፈ ወዲህ ነገሮች እንደ በፍቱ አይደለም፤ አንድ ሰው መሥዋዕት አንደ ብቻ ነው የቀረበለት ይህም አንደ ኢየሱስ በመስቀል በከፈለው ዋጋ። ታዲያ አንድ አማኝ መስዋዕት አንዴ ከተደረገለት ከክርስቶስ መሥዋዕትነት ውጭ ለላ መሥዋዕት መጠበቅ የለበትም።
እንደ ብሉይ ክዳን ሀጢአት ከሰራሁ የሚያስተሰርይለት ዳግም መሥዋዕት የለም።
ከዚህ መሥዋዕት በላይ አልፎ በሀጢአተ የመኖርን ሰው ቃሉ ''የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ የጸጋውን መንፈስ ያክፋፋ '' ይለዋል ለዚህም እግዚአብሔር ትልቅ ቅጣት እንዳዘጋጀለት ነው ቃሉ ምናገረን።
እግዚአብሔር ልጁን ለእኛ ሀጢአት ብሎ ጨክኖበት እየመረረውም ለሀጢአት አሳልፎ ሰጥቶአልና በልጁ ጉዳይ ድርድር አይቀመጥ ልጁን የተላለፈ ለእግዚአብሔር ቀዩን መስመር አልፏል አይራራለትም። ልጁን አቅልለን ሲናየው እግዚአብሔርን አያስችለውም ወድያውኑ ይነሣል፤ ምክንያቱም ለዛ ሰው ያለ ሀጢአት ወርዶ ተሰቅሎ ሞቶለታልና ።
እግዚአብሔር በልጁ ጉዳይ ቀልድ አያውቅምና ቀይ መስመሩን አንለፍበት!!
ይቀጥላል ....
✍️አማኑኤል ነጋሽ(አቡ)
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |