ለምን ነጋ?
በደስታ አገር ውሰጥ መሀል ክፍለ ከተማ፣
ብርሃኑን አድምቆ የ ፍቅራችን ሻማ፣
ደስ እያላቸው ሰማይና ምድር፣
እንደ አሳ ሰጥሜ በምኞቴ ባህር፣
ባማረው አዳራሽ ሰፍሬ በእንቅልፌ፣
ከናፍቆቴ ጉያ ሃሳቤን ታቅፌ፣
ልኑር ስል ይህ ፍጥረት አቤት ግን ቅናቱ!
ምሽት ይሻለኛል ለምን ነጋ ሌቱ?
ሁሉም ከተሟላ ቀን ከሆነ ሁሌ
መች ታስቦ ያውቃል ፈጣሪ እንዳለ?
በተደላው አለም እንድያው ስንደላቀቅ፣
ቅጠሉን ጠግቤ ከፍሬው ግን ብርቅ፣
ጥርሴ ይሳቅ እንጂ ውስጤ የለውም ጤና፥
ምሽት ይሻለኛል እረፍት አለውና።
ለምን ነጋ ሌቱ ልኑር ስል ህይወቴን?
እርካታን ጠግቤ ሳልሸኘው ጥማቴን።
አይኔ በቃኝ ሳይል እንባ ማፍሰሱን ፣
ጉልበቴ ሳይደክም ሳያቆም መንበርከኩን።
ምረባውን ማይረባውን ሁሉን ባንዴ ይዞ፣
ልቤን ልያደናብር ሊያስቀረው አፍዝዞ፣
ቀኑ ለምን መጣ አልፈልገውም እኔ፣
ምሽት ይሻለኛል አይይ ብርሃንን አይኔ።
✍አላዘር T.
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
በደስታ አገር ውሰጥ መሀል ክፍለ ከተማ፣
ብርሃኑን አድምቆ የ ፍቅራችን ሻማ፣
ደስ እያላቸው ሰማይና ምድር፣
እንደ አሳ ሰጥሜ በምኞቴ ባህር፣
ባማረው አዳራሽ ሰፍሬ በእንቅልፌ፣
ከናፍቆቴ ጉያ ሃሳቤን ታቅፌ፣
ልኑር ስል ይህ ፍጥረት አቤት ግን ቅናቱ!
ምሽት ይሻለኛል ለምን ነጋ ሌቱ?
ሁሉም ከተሟላ ቀን ከሆነ ሁሌ
መች ታስቦ ያውቃል ፈጣሪ እንዳለ?
በተደላው አለም እንድያው ስንደላቀቅ፣
ቅጠሉን ጠግቤ ከፍሬው ግን ብርቅ፣
ጥርሴ ይሳቅ እንጂ ውስጤ የለውም ጤና፥
ምሽት ይሻለኛል እረፍት አለውና።
ለምን ነጋ ሌቱ ልኑር ስል ህይወቴን?
እርካታን ጠግቤ ሳልሸኘው ጥማቴን።
አይኔ በቃኝ ሳይል እንባ ማፍሰሱን ፣
ጉልበቴ ሳይደክም ሳያቆም መንበርከኩን።
ምረባውን ማይረባውን ሁሉን ባንዴ ይዞ፣
ልቤን ልያደናብር ሊያስቀረው አፍዝዞ፣
ቀኑ ለምን መጣ አልፈልገውም እኔ፣
ምሽት ይሻለኛል አይይ ብርሃንን አይኔ።
✍አላዘር T.
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |