ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ
#ሁለት_ሰይፍ
✍️ሜርሲ
ክፍል አንድ
"ይሄ መኪና ፍጥነቱ ምንም አላማረኝም::"
"ሆስፒታል ገብታለች እኮ ልጄ::"
"አውቃለሁ ግን ተረጋግተህ ንዳው..."
ወደ ኋላ ስትመለከት ማክቤል ጆሮው ላይ ማዳመጫ አድርጎ ውጪውን ይመለከታል::
ዘወር ትላለች:-
"መኪናውን አቁመው.."
ዞሮ ይመለከታታል:-
"ምን ሆነሻል::"
"መኪናውን አቁመው.."ድምፁአን አውጥታው ስለነበር ማክቤል ማዳመጫውን ያወጣ እና ወደ እነርሱ ይመለከታል::
"ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም::"
"እማዬ..."
ሁለቱም ወደ ማክቤል ይዞራሉ::እና በዝግታ አይናቸውን ከማክቤል አይን ጋር አከታትለው ከመንገዱ ያደርጋሉ::
"ፍፁም እያየህ::" ከእሷ ድምፅ እኩል መሪውን ወደ ግራ ያዞረዋል::
"እማ... አባ..."ሳራ በሩን በርግዳ ትገባ እና አልጋው ላይ የመዝለል ያህል ወጥታ ከጉያዋ ውስጥ ታስገባዋለች::
"ቅዠት ነው.... ቅዠት ነው::"
* * *
"እግዚአብሔር በሥራው አይሳሳትም::የሚሳሳት ይመስላል በእርግጥ::ግን እውነታው እሱ ዘንድ ስህተት የለም::"ፕሮግራሙ አልቆ ሰዉ መበተን ጀምሮ ሳለ አንድ ረዘም ብሎ መልከ መልካም ወጣት እየተጣደፈ ጉባኤውን ቀድሞ ይወጣል::
"ናቲሻ.."
ዘወር ብሎ ይመለከታል::
"አንተ... ወዴት እያመለጥክ ነው::"
ቆም ብሎ በፈገግታ ይጠብቀው እና ሞቅ ያለ ሰላምታ ይለዋወጣሉ::
"ተናፍቀሃል.."
"እዚህም እንደዛው::"
"እና ምን ያስሮጥሃል..."
"ትንሽ ደክሞኛል አቤኒ::እዚህ ቆየሁ ማለት ጉባኤውን ሁሉ ሰላም አልኩ ማለት ነው::"
"ይሄ መበላሸት ነው ይታረም::"
"በእርግጥ አዎ ይታረማል::"
"ሙሉ ፕሮግራሙን ተኝተሽ ነበር..."
"ሲጀመር ለአንቺ ስል ነው የመጣሁት.."
ሁለቱም ድምፁን ወደ ሰሙበት ዘወር ይላሉ::ሁለት ሴቶች እና አንድ ልጅ ፈጠን እያሉ ጀርባቸውን ሰጥተው ከግቢው ያልፏቸዋል::
"ታሳዝነኛለችም... ታበረታኛለችም::"
ናትናኤል ወደ እሱ ይዞራል:-
"ማናት.."
"አንተ ውጭ በነበርክ ጊዜ ብዙ ታሪክ አልፎሃል::"
ናትናኤል ድጋሚ ዞሮ ይመለከታቸዋል::
"እንዴ... ናቲ... መች መጥተህ ነው?"
"አላልኩህም... ማደሬ ነው በቃ::"
"የቅዱሳን ሰላምታ ሊናፍቅህ ነበር የሚገባው::ምሳ እና ቡና በእኔ ግብዣ ይሁን::አሁን ሰላም በላቸው::"
ፈገግ ብሎ ወደጠራው ሰው ዘወር ይላል::
* * *
"መኪናዬን በትክክል እንድነዳው ፍቀጂልኝ እባክሽ::"
"ምኑን ነዳሽው::እስካሁን በእግሬ ሮጥ ሮጥ ብል ቤት ደርሼ ወጥቼ ነበር::"
"በዚህ ሰዓት ክራውድድ ይሆናል::ሶ ታገሺኝ ፕሊስ::ደግሞ የት ነው የምትወጪው?"
"የጓደኛዬ ልደት አለብኝ::"
"የአንቺ ጓደኞች ደግሞ በየእሁዱ ነው እንዴ ልደት የሚያከብሩት::"
"ጓደኞቼ ብዙ ናቸው::ሰው ይስጥሽ ብሎ መርቆኝ::ዛሬ ልክ አልሰራሽም::ቆይ የከተማው ሰው ሁሉ እኔ ሳልሰማ መኪና ታደለው እንዴ::"
ሳራ ፈገግ ብላ መንገዱን ታያለች::
"በኢየሱስ ስም!" ቃሉ ከአፏ እንደወጣ ፍሬኑን የበጠሰ መኪና ከግራ በኩል በብርሃን ፍጥነት ወጥቶ ከአንዱ ቪ8 ጋር ይላተማል::ሁለቱም በድንጋጤ ፈዘው ከፊታቸው የተፈጠረውን እየተመለከቱ ከኋላ ድምፅ ይሰሙ እና ዘወር ይላሉ::
"ማክ.." በአንድ ድምፀት::
* * *
ሁለቱም ማክቤል ላይ ዓይናቸውን አድርገው ከአልጋው ጫፍ ተቀምጠው ይመለከቱታል::
ዮሃና በዝግታ ትነሳለች::
"ተኝቷል::ልሂድ::" ቀረብ ብላ ግንባሩን ትስመው እና ለአፍታ ተመልክታው ትወጣለች::ሳራ ትከተላታለች::በሩን ገርበብ ካደረገች በኋላ ዮሃና ክፍሏ ስትገባ ተከትላት ትገባለች::ዮሃና ቁም ሳጥኗን በመክፈት በፍጥነት ልብስ ለመምረጥ ትሞክራለች::ከአልጋው ላይ ከዘረገቻቸው ልብሶች ላይ ግራ በመጋባት አይኗን ታንከራትታለች::
ከበሩ ላይ ቆማ ወደ ምታያት ሳራ እየተመለከተች:-
"ስምኚ እህቴ.... እኔ ስቻኮል ምን መልበስ እንዳለብኝ እንኳ አላውቅም::"
"እኔ ገና እንድትሄጂ አልፈቀድኩልሽም::"
"ቸርች ሄጄልሻለሁ ይሄን አትርሺ::"
"ለእኔ ነበር..."
"ኦፍ ኮርስ...ወንበር ላይ ከምተኛ አልጋዬ ላይ ተኝቼ አሳልፌ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ ጣጣ ባልተከተለ ነበር::አሁን አትመርጪልኝም::ህ.. ለዛሬ ብቻ::"
ወደ እሷ ስትቀርብ በደስታ ከመሬቱ ዘለል ዘለል ትላለች::
"ማክ ተኝቷል..."
"ኦህህ... ይቅርታ...." ባለችበት ቀጥ ብላ ትቆማለች::
ሳራ አልጋው ላይ ካሉት ልብሶች አንዱን ውሃ ሰማያዊ ከለር ቀሚስ ታነሳለች::
"ትራይ ዚስ ዋን..."
ዮሃና በፈገግታ ትቀበላታለች::
"ግን እባክሽ... አምሽተሽ እና ሰክረሽ ቤት አለኝ ብለሽ እንዳትመጪ::"
"አያሳስብሽ..ቤት ሞልቷል..."
"ህ..."
"አልጠጣም.. አላመሽም እህቴ::"
"ሹፌሩን ልደውልለት::"
"አይ እህቴ.... ራይድ እደውላለሁ::"
በትዝብት ስትመለከታት ቆይታ ትወጣለች::
* * *
ሳራ ከእንቅልፏ ስትባንን ከሶፋው ላይ ከሳሎኑ መተኛቷን አስተዋለች::ስልኳን ከጠረጴዛው በማንሳት ስትመለከት ከምሽቱ አንድ ከአስር ይላል::
"በጌታ... እንዴት ብተኛ ነው..." አሰብ ታደርግ እና እግሯን በፍጥነት ከሶፋው በማውረድ ነጠላ ጫማውን አድርጋ ስልኳን እንደያዘች ወደ ላይ በደረጃው ትወጣለች::ደረጃው እንዳለቀ አንደኛ ፎቅ ላይ ካለው በስተቀኝ በኩል የማክቤልን ክፍል ከፍታ ትገባለች::አይኖችዋን ከክፍሉ ላይ እያንከራተተች ከቆየች በኋላ ከፍ ባለ ድምፅ:-
"ማክቤል..."ትላለች::
Like🥰 Comment📩 Share💫
ቀጣዩ እንድለቀቅ
ይቀጥላል...
@gitim_alem