ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ
#ሁለት_ሰይፍ
ክፍል ሁለት(ሜርሲ✍️)
"ማክቤል.." በዝግታ ዘወር ብሎ ይመለከታት እና ዓይኑን አንገቱን ይመልሳል::በእፎይታ ትተነፍስ እና ከሶፋው ላይ ከአጠገቡ ትቀመጣለች::
"ጨረቃዋ ደስ ትላለች አይደል?"
"እማዬ ሁሌ ማታ ማታ እዚህ መቀመጥ ትወድ ነበር::"
ትመለከተዋለች::
"ለምን ቆንጆ እራት አንሰራም?"
"ላዛኛ ነው?"
"ኦፍኮርስ.... የፈለግከውን::"
እጁን ይዛ ይነሳሉ::
* * *
"እና አቤኒ... እንዴት ነው ቸርች... የወጣቶች መሪ መሆን..."
"ለአንተ አልነግርህም መችም ፈታኝ መሆኑን ::ግን እግዚአብሔር ይመስገን እሱ ከድካምህ በላይ ያደርግሃል::"
"እሱ ነው ትልቁ ነገር::" አስተናጋጁ ያዘዙትን የቤቱን እስፔሻል ኮምቦ ከፊታቸው ያስቀምጥ እና ከመሶቡ ከትሪው ላይ አድርጎላቸው::
"መልካም እራት::"ብሏቸው ሲሄድ አፀፋዊ ምስጋናቸውን ሰጥተውት ወደ ምግቡ ይመለከታሉ::
"በጣም የናፈቀኝ ምግብ::"
"ምሳ መጋበዙ ባይፈቀድልኝም እራቱ አይቅርብኝ ብዬ ነው::እንፀልይ::"
"ያ.."አይኑን ሲጨፍን አቤነዘር ይፀልይ እና እየተጫወቱ መመገብ ይጀምራሉ::በመሃል ናትናኤል አሰብ ያደርግ እና:-
"እኔ ምልህ አቤኒ... የሚከራይ ቤት እየፈለግኩህ ነበር እና አሪፍ ደላላ የምታውቀው ካለ..."
"ለማን ነው የምትፈልገው?" ግራ እየተጋባ ጠየቀው::
"ለእራሴ ነዋ ሌላ ለማን ይሆናል::"
"አረ አትቀልድ ናቲ::ቤታችሁስ..."
"ጠብቄ ነበር አለማመንህን::online ሥራዎችን ስለሆነ እየሰራሁ ያለሁት እረጅም ሰዓት ቤት ስቀመጥ ሌላ ነገር ይመስላቸዋል::እና ሥራው ነፃነት ይፈልጋል::በዛ ላይ ደግሞ እራሴንም ብቻዬን ሆኘ ሕይወቴን መምራት እፈልጋለሁ::"
"ይሄ ከባድ ነገር ነው::ነግረሀቸዋል?"
"አይ::ቤቱን ላግኝ እና እነግራቸዋለሁ::"
"ካልክ እሺ.... እምም... ደላላ ሳያስፈልገው የሆነ ቤት አለ::ካላከራዩት የምጠይቅልህ ይሆናል::ግን ምን አይነት ቤት እንደምትፈልግ አልነገርከኝም::"
"ምንም ይሁን ብቻ የእኔ ቤት መዋል የሚያሳስበው ሰው የሌለበት ቦታ ይሁን::"
"ገባኝ.."
* * *
ሳራ ከሳሎኑ ላይ ካለው ሶፋ ላይ ጋቢ ለብሳ ጋደም ብላ አንዴ የግድጊዳውን ሰዓት አንዴ በሩን ትመለከታለች::ሰዓቱ ለስድስት ይቆጥራል::ስልኳን አንስታ ቁልፎቹን ስትጫን የበር ጥሪውን ትሰማ እና ብድግ ብላ የሳሎኑን በር ከፍታ በመውጣት ከግቢው በር እሮጥ ብላ ደርሳ በሩን ትከፍታለች::ዮሃና በስካር መንፈስ ሆና ራይድ ካመጣት ሹፌር ትከሻ ላይ እራሷን ጥላለች::
"እባክሽን ታግዥኝ::"
ሳራ ፈጠን ብላ ትደግፋት እና ጋቢውን ታለብሳታለች::
"እስከ ቤት ላግዝሽ?"
"አይ አመሰግናለሁ::ከፈለችህ?"
"አዎ::በዚህ እንኳ ጎበዝ ናት::"
ፈገግ ብላ:-
"አመሰግናለሁ::ደሕና እደር::" ይዛት እስክትገባ ይመለከት እና ወደ መኪናው ይመለሳል::"
ሳራ ደግፋት እያስገበቻት ዮሃና በጨረፍታ ትመለከታታለች:-
"እህቴ.. ይቅርታ::ሳልፈልግ ነው::"
"አስገድደውሽ ነው አይደል::"
"አዎ እህቴ ልክ... ብለሻል::"
"አስገድደውሽ.. ህ... ማክቤል ተኝቷል ድምፅሽን ቀንሽ::
ከተከፈተው በር ይገቡ እና ከኋላቸው ትዘጋለች::
* * *
ዮሃና ከፊቷ ላይ ያለው ብልድልብስ ሲከፈት አይኖችዋን ትከፍታለች::ወዲያው የእራስ ምታቱ ህመም ጭንቅላቷን በእጇ ያስይዛታል::ሳራ ቆማ ትመለከታታለች::
"እኔና መክቤል እየወጣን ነው::ሱፍ ፍትፍት እና ጁስ አዘጋጅቼልሻል::ማስታገሻም ውሰጂበት::ዛሬ እረፍት አድርጊ::"
"እንዴ.. ክላስ እሄዳለሁ እኮ..."
"እንደዚህ ሆነሽ ነው የምትሄጂው!?.. ማታ ደም ነበር እኮ ሲያስመልስሽ የነበረው::ለማንኛው ሰራተኞቹን ቦታ ቦታ አስይዤ እመለሳለሁ::ሀኪም ቤት እንሄዳለን::"
"ሀኪም ቤት..!?"
ሳራ ሳትመልስላት ትወጣለች::
"ኤጭጭ ..."
* * "
"ሰዓት እየሄደ ነው... ቶሎ በይ..."
"እየጨረስኩ ነው እህቴ....."
የበሩን ደውል ስትሰማ ግራ በመጋባት አሰብ ታደርግ እና ወደ ውጭ በመውጣት በሩን ስትከፍት ከፊቷ የቆመውን ወጣት አይታ ደንገጥ ትላለች::
"ሰላም.. ምን ነበር?"
"ሰላም... ናትናኤል እባላለሁ::የሚከራይ ቤት እንዳላችሁ ሰው ጠቁሞኝ ነው የመጣሁት"
Like🥰 Comment📩 Share💫
ቀጣዩ እንድለቀቅ
ይቀጥላል...
@gitim_alem