🔴 ዓሹራን መፆም እንዳንዘነጋ
ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል ""ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው “በጉጉት ጠብቀው” ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! ብለዋል።
ነቢዩም(ሰዐወ) "የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ከአላህ እጠብቃለው" ብለዋል።
📍 ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው??
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ተጠቅሷል። ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከበባዶችንም ጭምር የሚለውን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል:-
" የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን""
📍 ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን?
እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።
የዘንድሮ ዓሹራ የሚሆነው ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ሙሐረም 10 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሀምሌ 9 2016 ወይም July 16 ሲሆን ከፊቱ ሰኞን ወይም ከኋላ ረቡዕን አብሮ መጾም ተገቢ ነው።
አላህ ይወፍቀን!