የቲኬት ብር ተመላሽ ስለማድረግ
•••••••••••••••••••••••
ለመስከረም 15/2015 ዓ/ል "በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር እና በዑለሞቻችን መንገድ ሕያው ነን" በሚል መሪ ቃል 3ኛ ዙር ታላቅ ሀገር አቀፍ መውሊድ ለማዘጋጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት በደብዳቤ ቁጥር አአከፅ17/30.4/89 ህጋዊ ፍቃድ ከተሰጠን በኋላ፣ ከህገ ወጡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተፃፈ ደብዳቤን መነሻ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመስከረም 12/2015 ፕሮግራሙ የፀጥታ ችግር ያጋጥመዋል በሚል ፈቃዱን መሰረዙ ይታወቃል።
ማህበራችንም ህጋዊ አካሄዶችን ተከትሎ ከጨረሰ በኋላ ከአዲስ ፓርክ/ሚሊኒየም አዳራሽ አስተዳደር ጋር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላቶች ጋር የውል ስምምነት በመግባት አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም ለማህበረሰባችን በማሳወቅ የቲኬት ሺያጭ ከጀመርን በኋላ ታላላቅ የሀገራችን ዓሊሞች/የእምነቱ አስተምህሮ አዋቂዎች ጠርተን ወደ ከተማችን ከገቡ በኋላ በቀን መስከረም 12/2015 ከአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከሰዓት በኋላ በተደረገልን ጥሪ መሰረት ፕሮግራሙን ማካሄድ እንደማንችል በቃል የተነገረን ሲሆን ክልከላው በደብዳቤ እንዲገለፅልን እና ህዝባችንን እንድናሳምን አጥበቀን የጠየቅን ቢሆንም ክልከላው ከቃል በዘለለ በደብዳቤ ሳይገለፅን አልፏል።
በወቅቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ :_ ጊዜው የደመራ እና የእሬቻ በአል የሚከበርበት በመሆኑ የፀጥታ ሃይል ልንመድብላቹህ አንችልም። ከመስከረም በኋላ ባለው ጊዜ በምትፈልጉት ቀን ጠይቁን እንተባበራችኋለን ብለው ቃል ገብተውልን የነበረ ቢሆንም ቀኑ ካለፈ በኋላ ቃሉ በተግባር ሊፈፀም አልቻለም። ለአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ለጥቅምት 6፣ 13 እና 27 መውሊዱ እንዲፈቀድልን አበክረን በየእለቱ ደጅ እየጠናን የጠየቅን ቢሆንም ከበላይ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረን እናሳውቃችኋለን እያሉ ለጥቅምት 6 እና 13 ያቀረብነውን ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡን ወደ ጥቅምት 27 ለማዞር ተገደድን። ከጥቅምት 15 በኋላ ባለው ጊዜ በየትኛውም ቀን አንድ ቀን እንፈቅድላችኋለን ብለው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቃል የገቡልን ቢሆንም ደብዳቤ አስገብተን ለጥቅምት 27 እንዲፈቅዱልን ስንጠይቅ ግን ቃላቸውን አጥፈው መልሰው እንደማይፈቅዱ ገለፁልን።
የመስከረም 15 መውሊድ ሲሰርዙ መስቀልና እሬቻን አሳበው የፀጥታ ችግር ስላለ ነው ብለው ሲናገሩ የነበሩ የመንግስት ኃላፊዎች መስከረም 15 ካለፈ በኋላ ግን ጉዳዩ ከፀጥታ ችግር ጋር የተገናኘው ህገወጡ የአዲስ አበባ የወሃቢያ መጅሊስ በፃፈው ደብዳቤ ምክንያት መሆኑን እና ከአዲስ አበባ የወሃቢያ መጅሊስ ደብዳቤ እንድናመጣ ከወሃቢያ መጅሊስ ጋር ተባብረን እንድንሰራ በግልፅ መናገር ጀመሩ። ማህበራችን ቀድሞውንም ቢሆን የጸጥታ ችግር የሚባለው ለሽፋን እንጂ ዋናው ሰበብ ለወሀቢያ መጅሊስ እውቅና እንድንሰጥ ለማስገደድ እንደነበር ግዛቤ ወስዶ ነበር።
የሚሊኒየሙ አዳራሽ መውሊድ ከጥቅምት 27 በኋላ እንደማይሳካ ስናውቅ ቲኬት ለገዙ 2ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የአዳራሽ ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስበን የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች እስካሁን ማሳካት ባለመቻሉ በቲኬት ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ወደ ህዝብ ተመላሽ መደረግ ስላለበት ይህን ፅሁፍ መልቀቅ አስገዳጅ ሆኗል። በመሆኑም ለመስከረም 15 መውሊድ ቲኬት የገዛችሁ ሙሂቦች ከነገ ማክሰኞ ህዳር 13/2015 ጀምሮ ፒያሳ አትክልት ተራ ከሊፋ ህንፃ አጠገብ የሚገኘው ሴካ ህንፃ 10ኛ ፎቅ የማህበራችን ቢሮ በመምጣት ቲኬት የገዛችሁበትን ብር ተመላሽ እንድትወስዱ እንጠይቃለን። ተመላሽ ለመጠየቅ ሲመጡ የገዙትን ቲኬት ይዘውልን ይምጡ።
ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ ለማድረግ በጊዜ በገንዘብ በእውቀትና በጉልበታችሁ ላገዛችሁን እንዲሁም መውሊዱን ለመታደም በጉጉት ስትጠብቁ ለነበራችሁ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ በተፈጠረው ጊዜያዊ ጫና መውሊዱ ሊካሄድ ባለመቻሉ አጅግ በጣም በትልቁ ይቅርታ እንጠይቃለን።