🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
👉ክፍል አንድ👈
👉ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን
፩. አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት #ጥንተ_አብሶ እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል፡
++++++++++++++++++++++++++++++
፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ #እግዚአብሔር_ዘርን_ባያስቀርልን_ኖሮ_እንደ_ሰዶም_በሆንን_እንደ_ገሞራም_በመሰልነ_ነበር ኢሳ 1፥9 ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት #ድንግል_ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ክታቡ #የአብራሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 1፥17 በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳይያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት #እመቤትችንን ነው #አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት።
++++++++++++++++++++++++++
፩.፪ ነብዩ ዳዊት #የወርቅ_ልብስ_ተጎናጽፋና_ተሸፋፍና_ንግስቲቱ_በቀኝህ_ትቆማለች_ልጄ_ሆይ_ስሚ_እይ_ጆሮሽንም_አዘንብይ_ወገንሽን_የአባትሽን_ቤት_እርሺ_ንጉሥ_ውበትሽን_ወዶአልና መዝ 49፥9-11 ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ተጎናፅፋ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ #ንጽሓ_ነፍስ_ንጽሃ_ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ 1፥1 ንጉሥ የተባለ ልጇ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሲሆን ውበትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው፡፡
+++++++++++++++++++++++++++
፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን #ወዳጄ_ሆይ_ሁለንተናሽ_ውብ_ነው_ነውርም_የለብሽም መኃ4፥7 ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹሕ ነው ብሎ አመስግኗታል፡፡
፪. የቅዱስ ገብርኤል ብሥራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ #የዘር_ኃጢአት እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን
#ጸጋን_የሞላብሽ_ሆይ_ደስ_ይበልሽ_ጌታ_ካንቺ_ጋር_ነው_አንቺ_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ" ሉቃ 1፥28
++++++++++++++++++++++++
፪.፩ #ጸጋ_የሞላብሽ_ሆይ እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት #እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው #ሁሉም_የእግዚአብሔር_ክብር_ጎሎአቸዋል ሮሜ 3፥24 እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሠሩ አይደለም ነገር ግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው #ኃጢአት_ባልሰሩት_ላይ_እንኳን_ሞት_ነገሰ ሮሜ 5፥14 ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ❓ ይህ በርግጥም #እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++
፪.፪ #ከሴቶች_መካከል - ሁለተኛው ነጥብ #ድንግል_ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጽ #ልዩነት_የለም_ሁሉ_ከበደል_በታች_ናቸው ሮሜ 3፥22 ይላል።ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም #ወላዲተ_አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ። #እመቤታችን ክብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን❓ አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽሕት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ፡፡
++++++++++++++++++++++
፪.፫ #የተባረክሽ_ነሽ - በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል #ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው
⚡️በአጠቃላይ ድንግል #ድንግል_ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከሥጋዋ ሥጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለመሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት ወደፊት በቀጣዩ ክፍላችን የምንመለከተው ይሆናል፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1