🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
ክፍል ሁለት
⚡️፫. #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሐ ባሕርይውን መዳፈር ነው #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ሥጋና ነፍስን ከሰማይ ይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባሕርይ ተዋሕዶ ነው።#እንግዲህ_ልጆቹ_በሥጋና_በደም_ስለሚካፈሉ_እርሱ_ደግሞ_በሞት_ላይ_ስልጣን_ያለውን_እንዲሽር_እንዲሁ_ተካፈለ_የአብርሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 2፥14-15
+++++++++++++++++++++++++
👉እንግዲህ#ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው ሲሆን ሥጋንም ነፍስንም #ከድንግል_ማርያም ከነሳ እርሷ ደግሞ መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃጢአት ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ልንል ነውን ❓እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለት ነው ምክንያቱም ደፍረው #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ኃጢአት አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና #ይህ_ሰው_ኃጢአተኛ_መሆኑን_እኛ_እናውቃለን ዮሐ 9፥24
👉እኛስ #ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ሥጋ እንደነሳ እንመሰክራለን እንደ እውነተኞቹ አባቶቻችን #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን #ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን #ኦ_ድንግል_አኮ_ዘተአምሪ_ርስሐተ_ከመ_አንስት_እለ_እምቅድሜኪ_ወእምድሬኪ_አላ_በቅድስና_በንጽሕና_ስርጉት_አንቲ (#ድንግል_ሆይ_ካንቺ_አስቀድመው_ካንችም_በኋላ_እንደ_ነበሩ_ሴቶች_አደፍ_ጉድፍን_የምታውቂ_አይደለሽም_በቅድስና_በንጽሕና_ጸንተሽ_ኖርሽ_እንጂ ቅዳሴ ማር 5፥42
+++++++++++++++++++++++++
👉መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ #ከጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን መርገም ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል።
👉፩. የድንግል ማርያም ሥጋ የውርስ ኃጢአት ወይም የጥንተ አብሶ ፍዳ አለበት ከተባለ #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከርሷ ሲወለድ ኃጢአት የወረሰውን ሥጋ ወሰደ ሊባል ነው ❓ይህ ማለት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ነው ምክንያቱም #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ባሕርይ ኃጢአት ፈጽሞ አይስማማውምና ኃጢአት የነካውን ሥጋ ተዋሐደ ከተባለ መለኮት ኃጢአት ይስማማዋል እንደማለት ነው።ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ክህደት ነው ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች መመልከት ይቻላል
++++++++++++++++++++++++++++
?#ቅዱስና_ያለ_ተንኮል_ነውርም_የሌለበት_ከኃጢአተኞት_የተለየ_ከሰማያትም_ከፍ_ከፍ_ያለ ዕብ 6፥27
👉#ከኃጢአት_በቀር_በነገር_ሁሉ_እንደኛ_ተፈተነ………… ዕብ 4፥15
👉#ኃጢአት_ያላወቀውን_እርሱን_ስለኛ_ኃጢአት …2ቆሮ5፥20
👉፪. #የድንግል_ማርያም ሥጋ የጥንተ አብሶ ፍዳ ወይም የውርስ ኃጢአት አለበት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የማዳን ሥራ አለመቀበል ነው ። ምክንያቱንም ከዚህ እንደሚከተለው ማብራራት ይቻላል ።#የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከድንግል_ማርያም መርገም ያለበትን ሥጋ ከነሳ ክብር ምስጋና ይግባውና መርገም ባለበት ሥጋ መርገምን አራቀ ማለት በጭራሽ አያስኬድም። ይህ ደግሞ አለም እንዲድን የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበትም ምክንያት ከንቱ ሊሆን ነው ። የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበት ምክንያትኮ ሰው ሁሉ የመረገም የእዳ የበደል ተጠያቂ ስለነበር ንጹሕ የሚያድን በመጥፋቱ ነው።ለዚህም ነው በነብዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው?#እግዚአብሔር_አየ_ፍርድም_ስለሌለ_ተከፋ_ሰውም_እንደሌለ_አየ_ወደ_እርሱ_የሚማልድም_እንደሌለ_ተረዳ_ተደነቀም_ስለዚህም_የገዛ_ክንዱ_መድኃኒትን_አመጣለት_ጽድቁም_አገዘው ኢሳ49፥17
++++++++++++++++++++++++++++
🙏አዎን እግዚአብሔር ያጣው ንጹሕ ሆኖ ስለ ሌላው የሚማልድ ካሳ ቤዛ የሚሆን ሰው ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእዳ ከበደል በታች ስለነበሩ ንጹሕ መርገም የሌለበት ጠፋ ስለዚህም በንጹሐ ባሕርይው #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሕ ሥጋን ተዋህዶ ወደ እኛ መጣ ።ነብዩ የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ማለቱ እርሱ እራሱ ሰው ሆኖ አዳነን ማለቱ ነው ። እርሱ በባሕርይው ኃጢአት ስለማይስማማው ኃጢአት የሌለበትን ሥጋ ለመዋሐዱ ምንም ሊያከራክር አይችልም ።መርገም ያለበት መርገም ያለበትን ማዳን ቢችል ኖሮ ከብዙ ነብያት አንዳቸው አለምን ማዳን በተቻላቸው ነበር። #የድንግል_ማርያምን ንጽሕና በጥንቃቄ ከተረዳን ነገረ ድኅነትን እንዳናፋልስ ይረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው መሆን ሲገልጽ #ስለእመቤታችን ንጽሕና አስረግጦ የተናገረው #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19
#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው
👉ማብራሪያውን በክፍል ሶስት እንመለከታለን፡፡
+++++++++++++++++++++
ክፍል ሦስት ይቀጥላል
"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
+++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1