በየቀኑ ትለፋለህ...ትለፋለህ...ግን ብዙ የሚያስገርም ለውጥ የለህም አይደል? ስለ ቀርከሀ የምታውቅ ከሆነ ልፋትህን መቼም አታቆምም።
ቀርከሀን ውሀ ብታጠጣው፣ ማዳበሪያ ገዝተህ ብትንከባከበው ወይ አሪፍ የአየር ሁኔታ ውስጥ ብታረገው እንኳን በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት ብዙም አያድግም፤ አስገራሚው ነገር 5 አመት ከአንድ ወር ሲሞላው ግን ከ 5 ሜትር በላይ ቁመቱ ይመዘዛል። ለካ 5 ዓመት ሙሉ ለውጡን ያላየነው ረጅም ቁመቱን መሸከም የሚችል ስር መሬት ለመሬት እየዘረጋ ስለነበር ነው። አይታይህም እንጂ ጥረትህ ፅዋውን እየሞላ ነው! የልፋትህ ውጤት ሊከፈልህ ትንሽ እንደቀረህ እያሰብክ ጠንክረህ ተማር! ጠንክረህ ስራ!
💎ይህ ሀሳብ ለሚያስፈልጋቸው ወዳጆቻችሁ ሁሉ ሼር አድርጉ ቤተሰቦች💎
👇👇👇
ᴊᴏɪɴ ᴜs
@hebre_muslim @hebre_muslim