🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿
ኢትዮጵያ ውስጥ መቻቻል እንዳለ ለማሳየት ፖለቲከኛውም፣ ጋዜጠኛውም፣ አር ቲስቱም፣ አክቲቪስቱም፣ መሀይሙም፣ ምሁሩም እንቁጣጣሽ፣ ጥምቀትና ገና የሚያከብሩ "ሙስሊሞችን" ማቅረብ መጥቀስ የተለመደ ነው። በተቃራኒው የሙስሊም ዒዶችን የሚያከብሩ ክርስቲያኖችን ግን ሲያቀርቡ ወይም ሲጠቅሱ ገጥሞኝ አያውቅም። ለምን? ሙስሊሙ የእምነቱን ህግጋት ጥሶ የነሱን በአላት ማክበሩ ከመቻቻል ትርጓሜ ጋር ምን የሚገናኝ ነገር አለው?
እውነት ይሄንኑ የተንሻፈፈ አረዳድ መቻቻል አድርገው ካሰቡት ለምን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥለው ያቀርባሉ? እንዲህ አይነቱ "ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ሽሮ አበድሪኝ" አይነት የብልጠት ጨዋታ አይደብርም ወይ? ደግሞ'ኮ ሙስሊሙ የገዛ ወገኑን ከእንዲህ አይነት ተግባራት እንዲርቁ ሲያስተምር እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት ሊቆጥሩ ዳር ዳር ሲሉ ማየት ነው የሚገርመው።
✍IbnuMunewor
https://t.me/ibnukedir