Репост из: ግጥም ከብሩኬ አንደበት
•
አወይ መሸታ ቤት
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ደስ ያለው የደስታ እያለ ሲጋብዝ
ያዘንው ብቻውን ጠጥቶ ሲተክዝ
ሞቅ ያለው ሲጨፍር ተነስቶ በሆታ
የበቃው ሲወጣ ባሳር በጉተታ
ሌላው ሲበሻሸቅ ቃል እየሸጎጠ
ለቤቱ አዝማሪ ግጥም እየሰጠ
ሆድ ያባው በብቅል ጉዱን ሲዘረግፍ
ዝም ያለው ለወሬ ጆሮን ሲያሰፈስፍ
እከሌ እንዲ ሆነ
ሀገር እንዲ ሆነች
ዜናው እንዲህ አወራ
ሲባል በመሸታው ጨዋታው ሲደራ
ያየው የሰማውን ለጠጪው ሲነግር
ሁሉም ከየአፉ ያለውን ሲገብር
ልክ ነው አይደለም ሲጧጧፍ ክርክር
ከየፓለቲካ አያሌው ሲቃመስ
ደግፍ አትደግፍ ጎራው ሲወቃቀስ
ሃሜቱ እንደጉድ እንደ ውሃ ሲፈስ
ቂም የተያያዘ ነገር ሲመዛመዝ
ቅስሙን የተነካ ለዱላ ሲጋበዝ
አሳላፊ ሲባል መጠጡ ሲቀዳ
ገሚስ አይኑን ሲጥል ሲከጅል ኮረዳ
ተቀበል ሲባባል በጭብጨባ ሲያመሽ
እጅ ይዞ ተነሱ ትከሻ ሲፈተሽ
ለጉድ መንበሻበሽ
ለጉድ መረባበሽ
የሞላበት ቅኔ ከየዘርፉ ያዘለ
አወይ መሸታ ቤት
ምን ያማይወራ የማይታይ አለ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
አወይ መሸታ ቤት
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ደስ ያለው የደስታ እያለ ሲጋብዝ
ያዘንው ብቻውን ጠጥቶ ሲተክዝ
ሞቅ ያለው ሲጨፍር ተነስቶ በሆታ
የበቃው ሲወጣ ባሳር በጉተታ
ሌላው ሲበሻሸቅ ቃል እየሸጎጠ
ለቤቱ አዝማሪ ግጥም እየሰጠ
ሆድ ያባው በብቅል ጉዱን ሲዘረግፍ
ዝም ያለው ለወሬ ጆሮን ሲያሰፈስፍ
እከሌ እንዲ ሆነ
ሀገር እንዲ ሆነች
ዜናው እንዲህ አወራ
ሲባል በመሸታው ጨዋታው ሲደራ
ያየው የሰማውን ለጠጪው ሲነግር
ሁሉም ከየአፉ ያለውን ሲገብር
ልክ ነው አይደለም ሲጧጧፍ ክርክር
ከየፓለቲካ አያሌው ሲቃመስ
ደግፍ አትደግፍ ጎራው ሲወቃቀስ
ሃሜቱ እንደጉድ እንደ ውሃ ሲፈስ
ቂም የተያያዘ ነገር ሲመዛመዝ
ቅስሙን የተነካ ለዱላ ሲጋበዝ
አሳላፊ ሲባል መጠጡ ሲቀዳ
ገሚስ አይኑን ሲጥል ሲከጅል ኮረዳ
ተቀበል ሲባባል በጭብጨባ ሲያመሽ
እጅ ይዞ ተነሱ ትከሻ ሲፈተሽ
ለጉድ መንበሻበሽ
ለጉድ መረባበሽ
የሞላበት ቅኔ ከየዘርፉ ያዘለ
አወይ መሸታ ቤት
ምን ያማይወራ የማይታይ አለ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel