Репост из: ግጥም ከብሩኬ አንደበት
•
ይግለፅሽ ብዕሬ
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ምን ብዬ ልጀምር
እንደምን ልግለፅሽ
ቃል አጣው እናቴ ላንቺ የሚሆንሽ
ለአብራክሽ ክፋይ ሞተሽ የምትኖሪ
በሰሀን ለሠጠሽ በቁና ሰፋሪ
ያንቺ ልፋትማ ሽልማት አይበቃው
የንግስቶች ካባ
ፍቅርሽን ላውራ ብል ይቀድመኛል እንባ
እማዬ እማአለም አያውቅሽ ኩነኔ
አንቺው ነሽ ያለሺኝ ከእግዜር በታች ለኔ
ሰዎች ፍቅር ብለው ደርሰው ቢሯሯጡ
ከእናት በላይ ፍቅር ከወዴት ሊያመጡ
ዘመን የማይሽረው የማይኖረው አቻ
የእናት ፍቅር ብቻ !!!
አዎ እናት አለም ለስቃይሽ ዋጋ
ክፍያ እንደሌለው
የወለድሽው ልጅሽ ዬሄን አዋቂ ነው
እንዳይርበኝ ርቦሽ እንዳይጠማኝ ጠምቶሽ
ይደግልኝ ስትይ ደምሽ ጠብሏል
ውለታሽን ዛሬ
ያጠባሽው ጨቅላ አድጎ ይመሰክራል
ዘውድ ነሽ እናቴ ሁሌም የምወድሽ
ከስኬቴ በላይ ዘውትር የማኖርሽ
መስዋት ከፍለሻል ተመን የማይኖረው
እድሜ ልኬን ብኖር ከፍዬ ማልችለው
ፍቅርሽ ቀለቤ ነው ባንቺነት ነው ክብሬ
ያንቺን ገደልማ ባይገልፀውም ቃሌ
ልፃፍ በጥቂቱ ትንሽ ጀማምሬ
ቢያቅተውም አፌ ይግለፅሽ ብዕሬ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
ይግለፅሽ ብዕሬ
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ምን ብዬ ልጀምር
እንደምን ልግለፅሽ
ቃል አጣው እናቴ ላንቺ የሚሆንሽ
ለአብራክሽ ክፋይ ሞተሽ የምትኖሪ
በሰሀን ለሠጠሽ በቁና ሰፋሪ
ያንቺ ልፋትማ ሽልማት አይበቃው
የንግስቶች ካባ
ፍቅርሽን ላውራ ብል ይቀድመኛል እንባ
እማዬ እማአለም አያውቅሽ ኩነኔ
አንቺው ነሽ ያለሺኝ ከእግዜር በታች ለኔ
ሰዎች ፍቅር ብለው ደርሰው ቢሯሯጡ
ከእናት በላይ ፍቅር ከወዴት ሊያመጡ
ዘመን የማይሽረው የማይኖረው አቻ
የእናት ፍቅር ብቻ !!!
አዎ እናት አለም ለስቃይሽ ዋጋ
ክፍያ እንደሌለው
የወለድሽው ልጅሽ ዬሄን አዋቂ ነው
እንዳይርበኝ ርቦሽ እንዳይጠማኝ ጠምቶሽ
ይደግልኝ ስትይ ደምሽ ጠብሏል
ውለታሽን ዛሬ
ያጠባሽው ጨቅላ አድጎ ይመሰክራል
ዘውድ ነሽ እናቴ ሁሌም የምወድሽ
ከስኬቴ በላይ ዘውትር የማኖርሽ
መስዋት ከፍለሻል ተመን የማይኖረው
እድሜ ልኬን ብኖር ከፍዬ ማልችለው
ፍቅርሽ ቀለቤ ነው ባንቺነት ነው ክብሬ
ያንቺን ገደልማ ባይገልፀውም ቃሌ
ልፃፍ በጥቂቱ ትንሽ ጀማምሬ
ቢያቅተውም አፌ ይግለፅሽ ብዕሬ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel