Репост из: ግጥም ከብሩኬ አንደበት
•
ችዬ ላላስቀርሽ
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ክረመቱ እየባሰ ውርጩ እየከበደ
ያዘለው ደመና ዶፍ እያወረደ
እደጅ አያስወጣ ብርዱ መከራነው
ይሄኔን እያየሽ ልሂድ የምትይኝ
ምን ብበድልሽ ነው?
ላንቺም አይመችሽ መንገዱ ጭቃ ነው
ለኔም አይመቸኝ ከሌለሽኝ አንቺ
ቅዝቅዝ ይልብኛል ጎጆዬ ኦና ነው
ትንፋሽሽ ካልሞቀው ገላዬ ባዳ ነው
ልንገርሽ ሂወቴ .....
ከጎኔ መሆንሽ ለኔ መኖሪያ ነው
ድምፅሽን ካልሰማው አይንሽን ካላየው
የለመደሽ ውስጤ ፍፁም ወዳቂ ነው
የምልሽ የለኝም የምለው ይሄው ነው
ከሰማሺኝ መቼም ካዘነልኝ ልብሽ
በጋው እስኪመጣ አይቁረጥ አንጀትሽ
ግዴለም የኔ አለም ክረምቱ እስኪወጣ
ካጠገቤ ሁኚ እንደው ልማፀንሽ
ክረምቱ በቃኝ ሲል አኔው ነኝ ምሸኝሽ
የምቴጂው መንገድ
ብዬ ጨርቅ ያልግልሽ
እንባ እያነቀኝ ሁነኛው ወዳጅሽ
ቆርጠሻል መሰለኝ ችዬም አልመልስሽ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
ችዬ ላላስቀርሽ
#ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ክረመቱ እየባሰ ውርጩ እየከበደ
ያዘለው ደመና ዶፍ እያወረደ
እደጅ አያስወጣ ብርዱ መከራነው
ይሄኔን እያየሽ ልሂድ የምትይኝ
ምን ብበድልሽ ነው?
ላንቺም አይመችሽ መንገዱ ጭቃ ነው
ለኔም አይመቸኝ ከሌለሽኝ አንቺ
ቅዝቅዝ ይልብኛል ጎጆዬ ኦና ነው
ትንፋሽሽ ካልሞቀው ገላዬ ባዳ ነው
ልንገርሽ ሂወቴ .....
ከጎኔ መሆንሽ ለኔ መኖሪያ ነው
ድምፅሽን ካልሰማው አይንሽን ካላየው
የለመደሽ ውስጤ ፍፁም ወዳቂ ነው
የምልሽ የለኝም የምለው ይሄው ነው
ከሰማሺኝ መቼም ካዘነልኝ ልብሽ
በጋው እስኪመጣ አይቁረጥ አንጀትሽ
ግዴለም የኔ አለም ክረምቱ እስኪወጣ
ካጠገቤ ሁኚ እንደው ልማፀንሽ
ክረምቱ በቃኝ ሲል አኔው ነኝ ምሸኝሽ
የምቴጂው መንገድ
ብዬ ጨርቅ ያልግልሽ
እንባ እያነቀኝ ሁነኛው ወዳጅሽ
ቆርጠሻል መሰለኝ ችዬም አልመልስሽ
✍@Lanchisel
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel