የልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
----
የካቲት 9/2017ዓ/ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
7ኛ ዓመት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የሰላም ኮንፈረንስ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) የልማት ተነሽዎች የልማት ተነሽዎች የሰላም ኮንፈረንስ ቀን ዩኒቨርሲቲው ከልማት ተነሽ አርሶ አደሮች በጋራ ጉዳዮች የሚመክርበት፣ ዩኒቨርሲተው እና ማህበረሰቡ በሰላማዊ የመማር ማስተማር፣ በልማት እና ዕድገት ተሳትፎ እና የልማቱ ተጠቃሚ በሚሆኑበት ዙሪያ ሀሳብ የሚለዋወጡበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች እና ቤተሰቦች የስራ ዕድል መፍጠሩን ጠቅሰው በቀጣይም የልማት ተነሽ አደሮች ተጠቃሚ በሚሆኑበት ዙሪያም በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሀን (ዶ/ር) በበኩላቸው የሰላም ኮንፈረንሱ ዓላማ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ግንኙነት ለማጠናከር፣ስለ ሰላም ለመምከር እና ከልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0WS2ippB2qdke7cKMkyqhoZhGar6WPCZXSynt8fYGN6WYG3sPRat6dXhNQhgsc2kul/?app=fbl