#ዐሹራእ_ደረሰ‼
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ዐሹራእ ምንድነው?
☞ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡
☞ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-
"ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡
#ለምን_ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡
እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡
የአላህ መልክተኛውም፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡ ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡
#ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡
የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡
#መጾሙ_ዋጂብ ነው ወይስ #ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሁክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡
ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
ዓኢሻህ(ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡
አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡
#መቼ_እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ሰኞ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱቱ አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ከ እሁድ-ማቅሰኞ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡
ለ. እሁድና ሰኞ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡
ሐ. ሰኞና ማክሰኞ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
መ. ሰኞን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ነው፡፡
አላህ ይወፍቀን
T.me/iqraknow t.me/iqraknow