አላህ በቁርኣኑ ከጠቀሣቸው ነፍሣትና እንሠሣት ምን ምን ትምህርት እንወስዳለን?
http://t.me/iqraknow
1 - ነምል (ጉንዳን ) ፡ (አን-ነምል ምዕራፍ ቁ- 18)
ተታሪነቷን እንኳን ወዳጅ ጠላት ይመሠክራል፡፡ ጉንዳኖች ብልጠታቸው ከጭንቅላታቸው፤ ጉልበታቸው ከመጠናቸው በላይ ነው፡፡ ማህበራዊ ኑሮአቸውንና የሥራ ወዳድነታቸውን የተመለከተ፣ በጠላት ላይ ያላቸዉን ትብበር ያስተዋለ በርግጥም ከነሱ ብዙ ትምህርትን ይማራል፡፡ ሱረቱ አን-ነምል ቁ-18 ን የከፈተ በአስደናቂ ንግግሯና ብሩህ እይታዋ ፈገግ ሣይል አያልፍም።
ከጉንዳን እነኚህን ትምህርቶች ውሰድ -
~ ክረምት በጋ ሣትል ጠንክረህ ሥራ፣
~ ለራስ ለወገንህ ሁን፡፡ እራስ ወዳድነትን ወዲያ በል፣
~ ከጉልበትም በላይ ብልሃት ይኑርህ፣
~ መረጃን በማስተላላፍና ስህተትን ለማረም ፍጠን።
ጉንዳን ትንሽ እንስሳ ነው። ዳሩ ግን ከክብደቱ 20 እጥፍ በላይ ሊሸክም የሚችል ነው።
በጣም ብዙ አይነት ዝርያዎች እያሉ የዝርያዎቻቸው ቁጥር ብቻ 22,000 የሚያሕል ነው። ከአንታርክቲካ በቀር፣ በየአህጉሩ እጅግ ይበዛሉ። በምድር ላይ ያሉት እንስሳት ክብደት ሁሉ ሲገመት፣ ጉንዳኖች ከክብደቱ ምናልባት 15-25 ከመቶ ይሆናሉ። 10 ኳትሪሊዮን ጉንዳኖች እንዳሉ ሲገመት ክብደታቸውም አጠቃለይ ከአለም ህዝብ እኩል ይሆናል።
በአንድ ጉንዳን ነገድ ውስጥ፣ ንግሥት ጉንዳን በጎጆው መሃል ዕንቁላሎችን ስታስቀምጥ ሠራተኞች ጉንዳኖች ምግብ ያምጣሉ። ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፤ሳንባ የላቸውም፤ሰራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል ንግስቶ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትችላለች:: እንዲያውም ባብዛኛው ዝርያ ሠራተኞቹም ሁሉ አንስት ናቸው፣ ጥቂት ብቻ የሚራቡ ወንዶች አሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg