Репост из: Shalom Positive thinkers ከእራስ ጋር
🎩
በድሮ ጊዜ አንድ #ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል።
ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት #ምርጫ አቀረቡለት።
• አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣
• አንድ #መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ ወይንም
• አምስት መቶ #ብር መክፈል፡፡
…
ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ «#ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው፡፡ ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት...፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ #ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፡፡ አልቻለም፡፡ ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና.....
.
«መቶ #ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡
«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
«በቃ አምስት መቶ #ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሳ፡፡
.
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መስራትህ ብቻ አይደለም፡፡ #ማሰብ_አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን #መናገር እንጂ #ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት። ይባላል
#ማስተዋሉን_ያድለን
via #ዳንኤል_ክብረት
🙋 🙋 🙋