የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች በሙሉ ወደ ገላን አባሳሙኤል ሊዘዋወሩ ነው።
***
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1174/2012 የተሰጠውን ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችለውን ሰፋፊ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነትም የህግ ታራሚዎችን የጥበቃና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት ለማሻሻል፣ የታረሙ፣ የታነፁና ህግ አክባሪ ዜጎች ሆነው ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ለማድረግ በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ ማዕከሎቹ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ማረሚያ ቤቶችን በመገንባት ታራሚዎችን ለአደጋ ሊያጋልጡ ከሚችሉ መጠለያዎች የማዘዋወር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፤አሁንም እየሰራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል፡፡
ስለዚህ ኮሚሽናችን በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ በመሆኑ የሀገር ውስጥም ሆናችሁ የውጭ ሚዲያዎች መረጃውን ለታራሚ ቤተሰቦችም ሆነ ለህዝብ እንድታደርሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡