በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍቺ እና የጉዲፈቻ ውሳኔዎች ምዝገባ ተጀመረ፡፡
******************************************************************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን የስራ ስምምነት ከፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋር ቀደም ብሎ ስምምነት መፈጸሙ ይታወቃል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም ዛሬ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም በይፋ አገልግሎቱን በአራዳ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች መስጠት ጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ፉዓድ ኪያር፣ የኢመደአ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አሰኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በአራዳ ምድብ ችሎት ተገኝተው መርሃ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን የተቋማት ቅንጅት ለከተማው አገልግሎት መሻሻል እጅግ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የምዝገባ ስርዓቱ ተደራሽ መሆን እንዲችል የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች በቅርቡ እንደሚተገበሩ ገልፀዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘውም አገልግሎት ፈላጊው የሚንገላታበትን አሰራር ማስወገድና አገልጋዩ ወደ ተገልጋዩ በመቅረብ የአገልግሎት ተደራሽነትንና የመረጃ ጥራትን መስጠበቅ ይኖርብናል ያሉ ሲሆን ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር በበኩላቸው ፍርድ ቤት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም በመሆኑ በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት ወደ ስራ መገባቱ የአገልግሎቱን ጥራት የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡ ክቡር አቶ ፉዓድ በንግግራቸው የጉዲፍቻ እና የፍቺ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚያልቁ በመሆናቸው የምዝገባ ስርዓቱ መጀመር ለተቋማቱ ብቻም ሳይሆን ጥራት ያለው መረጃ በማደራጀት ለሀገርም የሚሰጠው ጠቀሜታ የጎላ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከፍቺ እና ከጉዲፈቻ ምዝገባ በተጨማሪ የፋይዳ (ዲጂታል መታወቂያ) ምዝገባ በምድብ ችሎቶች የሚካሄድ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡