ምክር ቤቱ የሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን የስንብት ውሳኔን አጸደቀ
--------------------
( ዜና ፓርላማ ) ጥር 06 ፣ 2017 ዓ.ም.፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው የሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የስንብት ውሳኔን አጽድቋል፡፡
የስንብት ውሳኔውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸ-ገነት መንግስቱ አቅርበዋል፡፡
ዳኛ አዱኛ ነጋሳ እና ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የተጣለባቸውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ባለመወጣት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸውን ወ/ሮ እጸ-ገነት አብራርተዋል፡፡
የተሰጣቸውን ሹመት አላግባብ በመጠቀም፣ ዳኛ አዱኛ ነጋሳ ገንዘብ እና ቼክ በመቀበል ፤ ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የአስር ሚሊዮን ብር ቼክ በመቀበል ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት መፈጸማቸውን ሰብሳቢዋ ጠቅሰዋል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ ቋሚ ኮሚቴው ከፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጋር በጥልቀት እንደመከረበት ወ/ሮ እጸ-ገነት ተናግረው ፣ ውሳኔውን ምክር ቤቱ እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡
ውሳኔውን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን፣ “ቅጣቱ አስተማሪ አይደለም፤ አስተማሪ የሕግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ፤ ወደ መረጠን ሕዝብ ስንሄድ አገልግሎት እና ፍትህ የምናገኘው በገንዘብ ነው ስለሚሉን ውሳኔው ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡
በአንጻሩ፣ “ቋሚ ኮሚቴው ዳኞቹ ከመሰናበታቸው አስቀድሞ የፌዴራሉን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማዳመጥ ይገበዋል፤ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ውሳኔ እንደ ምስክር ተጠቅሞ ዳኞችን ከስራ ማሰናበት የዳኞቹን መብት ይጋፋል” የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡
በተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ ውሳኔው ውሳኔው ውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 5/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡
በመጨረሻም፣ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ፣ ሳምሶን መኮንንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ በአንድ ድምጸ-ተአቅቦ እና በአብላጭ ድምጽ አጽድቋል፡፡