ጉባዔው በ43 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ አቅጣጫ እና የውሳኔ ሐሳብ ሰጠ።
--------------------------------------------------------------------------
ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ተገቢው ምርመራ እና ጥናት ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 43 በሚሆኑት ላይ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።
በዚህም 38 የሚሆኑት የትርጉም አቤቱታዎች ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ጉባዔው ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በ3 አቤቱታዎች ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ እንዲቀርቡ እንዲሁም በአንድ አቤቱታ ላይ ደግሞ ተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥበት ጉባዔው አዝዟል።
በዕለቱ ጉባዔው ከተወያዬባቸው አቤቱታዎች መካከልም በመ/ቁ 6124/.. የተመዘገበ አቤቱታ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሞበታል በሚል የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ የውሳኔ ሐሳብ ተሰጥቶበታል።
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ