በአፍሪካ ትልቁ እና እጅግ ግዙፍ የሆነው መስቀል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቀበና ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም እየተገነባ ይገኛል
*******************************
በአፍሪካ ትልቁ እና እጅግ ግዙፍ የሆነው መስቀል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቀበና ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ይተከላል። 64 ሜትር ከፍታ ያለው የመስቀል ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዝግግት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ አእምሮ ምስጋናው እንደገለፁት 64 ሜትር ከፍታ ያለው ግዙፍ መስቀል ሲሆን በውስጡ ፓራናሚክ ሊፍት ይገጠምለታል። በዚህ ግዙፍ መስቀል ላይ 40 ሜትር ከፍታ ላይ መላው አዲስ አበባን የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል። በውስጡም ዓለም አቀፍ የጥናት እና ምርምር ማዕከል እንደሚገነባ የገለፁ ሲሆን ከተራራ ስር በግማሽ ተፈልፍሎ የሚሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊ ታሪክ የሚያስቃኝ ግዙፍ ሙዚየምንም እንደሚያጠቃልል ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ጎብኚዎች በቀጥታ እንዲከታተሉት የሚያስችል የአብነት ትምህርት ቤት እና ቤተ መፃህፍትን ያጠቃልላል።
እንደ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ አእምሮ ምስጋናው ገለፃ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆች የሚገነባ እና በሁለት ዓመታት ውሰጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ ለከተማ ከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ የሚያኖረው መሆኑ ተገልጿል። ለፕሮጀክቱ ጅማሮ የመሰረት ድንጋይ በብፁዕ አቡነ አረጋዊ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ተቀምጧል።