Репост из: ከመፅሐፍ ገፅ ®
የዘመድ ቄስ
በሀገራችን የዘመድ ቄስ እየፈታ ያልቅስ ይባላል። ሰው ሲሞት ካህናት ይጠሩና ፀሎት ያደርጋሉ። ይኼ ፀሎት > ይባላል ። ለካህኑ ፍትሐት ማድረግ የክህነት ግዴታው ነው። ካህን ሆኖ ምናልባት የተሰማራበት፡ምናልባት እንጀራው የሚበላበት፡ወይንም ደግሞ ስራው ነው። ምንም ቢሆን ግን ሟች ዘመዱ ነውና ያለፈ ህይወቱን፡ውለታውን፡ አብረው ያሳለፉትን፡መለያየታቸውን እያሰበ ያለቅሳል። ዘመድ መሆኑ እንዳይፈታ፡ ካህን መሆኑም እንዳያለቅስ አያግዱትም። ለዚህም ነው "እየፈታ ያልቅስ" የተባለው። ይህ አባባል ሁለት ነገሮችን አንድ አድርጎ የያዘ ነው። ስራን ወይም ኃላፊነትን እና ሰብአዊነትን ። መፍታት ስራው ነው። የተሰማራበት ግዳጁ። ማልቀስ ሰብአዊነት፡ሰው መሆኑ።ሰው በየትኛውም ሥልጣን ፡ክብር ላይ ሲቀመጥ በውስጡ ሰው መሆኑን መርሳት የለበትም ነገሮችን በሥልጣን ወይንም በእውቀት መነፅር ብቻ ማየት የለበትም። በሰብአዊነት ጭምር እንጂ። እርሱም ሰው ሆኖ የዚያኛውንም ወገን ሰውነት ሳይዘነጋ አንዳንዴም ራሱን በዚያኛው ጫማ ውስጥ ቆሞ ማየት አለበት።
ለሁላችንም ቢሆን የዘመድ ቄስ ያስፈልጋል።ኃላፊነቱን ሳይዘነጋ በሰብአዊነት የሚያገለግለን።
ሰሞኑን ያጋጠመኝ አንድ ታሪክ አካፊያቹ ልሰናበት ። በምሰራበት ክልኒክ አንድት እድሜዋ ከ13 የማይበልጥ ልጅ ለእርግዝና ምሪመሪያ መጣች ። በጣም ነበር የደነገጥኩት እንዴት በዚህ እድሜ ብዬ ስለ እሷ ማጣራት ጀመርኩ ይባስ ብሎ በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርታ እንደምትሰራ ነገሩኝ ። ከልብ አዘንኩ ማን ይሆን ለዚህች ልጅ ህይወት መበላሸት አላፊነት የሚወሰደው። ምን አይነትስ ወንድ ይሆን በዚህች ህፃን ጭኖች መሃል ገብቶ የሚደሰተው፡ የእሷን የስቃ ድምፅ መስማትስ እንዴት አስቻለው። በነገሩ በጣም ነው ያዘንኩት፡ ይህች ልጅ የዘመድ ቄስ ቢኖራት በዚህ ህይወት ጎዳና ውስጥ ባልተገኘች ነበር፡በየቤቱ በየ ሀገሩ እንደዚህች ልጅ የዘመድ ቄስ አጥተው የሚሰቃዩ ብዙ ህፃናት አሉ። ሁላችንም ቢሆን የዘመድ ቄስ መሆንም ሆነ ለኛ ለራሳችን ያስፈልገናል። ብዙ የዘመድ ቄስ የሚፈልጉ ሰዎች በዙሪያችን አሉ ፡የዘመድ ቄስ እንሆናቸው በማለት ጨርሳለው
ሰናይ ምሽት
rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad