s~ ሌላው ሰዉ ማክበር ራሴን እንደማክበር እቆጥረዋለሁ። በአንድ ሀሳብ ካልተግባባነው ሰው ጋር በሌሎች ብዙ ጉዳዮች አብሬው እሠራለሁ፣ እኖራለሁ።
~ ከአንድ ሰው አጥፍቶብኝና ተኮራርፈን ብዙም ሳልቆይ ሁሉን ረስቼ ፈገግ ብዬ ሠላምታ ሳቀርብለት ጥፋተኛው እኔ ነኝ ማለቴ አይደለም። ሕይወትን ያለሱ መኖር አልችልም፣ ራሴን ችዬ የቆምኩ አይደለሁም ማለቴም አይደለም።
~ ይህን የማደርገው ትህትና፣ ይቅር ማለት፣ ቂም አለመያዝ መልካም ሥራ እንደሆነ እስልምናዬ ስላስተማረኝ ነው።
~ አንዳንዶች ትዕግስትህን እንደ ፍራቻ ያዩታል፣
~ ይቅር ማለትህን ከድክመት ይቆጥሩታል፣
~ መልካምነትህን እንደ ሞኝነት ይመለከቱታል።
ግና
~ ሰዎች ምንም ይበሉ ምን ለሰዎች ብለህ የምትተወው መልካም ሥራ የለም። ለሰዎች እልህ ብለህ የምትሠራው መጥፎ ነገርም የለም።
~ አንድን በጎ ሥራ በሠራህ ቁጥር ቀልብህን መለስ ብለህ ታያለህ። ለአላህ ከሆነ ትቀጥላለህ። ለሰው ከሆነ ታቆማለህ።
~ ጥሩም ሥራ መጥፎ ሰዎች የሚሉትን አያጡም።
~ የሰውን ልጅ ሁሉ እኩል ማስደሠት ፈጽሞ የማይደረስበት ድካም ነው።
ሰላም ያዉለን
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏