የዘመን ቡትቶ፥ ለብሰን ከምንተኛ፤
የነጭ ለባሹ፥ ከምንኾን ጓደኛ፤
በፍርሐት ሐሩር፥ ለበቅ ከሚገርፈን፤
ምንም ካለመሥራት፥ ጉልበት እያጠረን፤
የዕድሜያችን መጃጀት፥
የዘመኑ ርዝመት፥ ሸክም ከሚፈጀን፤
አፍላነት ይሻላል፥
እንኳን አልጠወለግን፥ እንኳን አላረጀን!
የነጭ ለባሹ፥ ከምንኾን ጓደኛ፤
በፍርሐት ሐሩር፥ ለበቅ ከሚገርፈን፤
ምንም ካለመሥራት፥ ጉልበት እያጠረን፤
የዕድሜያችን መጃጀት፥
የዘመኑ ርዝመት፥ ሸክም ከሚፈጀን፤
አፍላነት ይሻላል፥
እንኳን አልጠወለግን፥ እንኳን አላረጀን!