በደረሰብህ የሕይወት መልካምም ኾነ መጥፎ ገጠመኝ የሕይወትህ መስመር ይቀየሳል። ትናንት የነበረ ታሪክህ ለዛሬ ማንነትህ መሰረት ነው። አንዳንዶች በሕይወትህ ላይ በፈጠሩት መጥፎ ጠባሳ ዛሬህ ላይ እየመጣ ቢያስቸግርህም "ትናንት አልፏል" ብለህ ልትተወው የምትችልበትን አቅም ይስጥህ ወዳጄ!
በትናንትህ ላይ ተመስርተህ ዛሬህን አታበላሽ፤ ሕይወት የራሷ መስመር አላት። መጥፎ መስለው ያለፉ ገጠመኞችህ የተፈጠሩት ከሌላ የባሰ መከራ ሊከልሉህ ነውና ክፉ ቢመስሉህ በቀልሕን ወደ ባሕር ወርውርና ሕይወትህን ምራ። ሁሉም ሰው አንድ አይደለም... ክፉ የመሰሉህም ወደ'ው ክፉ አልሆኑም፤ በደረሰባቸው ገጠመኝ እንጂ...
ስለዚህ ብትችል ዛሬን በትናንት፤ የዛሬ መልካሙን ሰው በትናንት ሌላ ሰው መዝነህ ልቡን እንዳትሰብር ተጠንቀቅ!
@amehasilassie