መሪዬ ነሽ!
.@amehasilassie
አያቴ ሲነግረኝ፥
"ድንጋይ እንደ ዳቦ እየተቆረሰ፤
የአዳም ዘር በሙሉ ከመናው አፈሰ፤
በቀደመው ዘመን፥ እግዚአብሔር ሲመለክ በሕገ ልቦና
የእስራኤል አምላክ፥ ሕዝቦችን ሊመግብ ከፀሐይ ሰማይ ላይ
አውርዷል ደመና።
.
በጨለመው ሌሊት ይነጋ ማይመስል
እንዲሕ አስባለሁ አንቺን አምሰለስል
ምንድነው መናውስ ምንድነው ሰማዩ
የወረደላቸው በዐይናቸው ዕያዩ፤
እንኳንስ መቀየር ድንጋዩን ወደ ሕብስት
ላመነ ይቻላል አምላክ ቃሉን አይስት...
.
"ላመነ ይቻላል!" እልሻለሁ እኔም በተከበረ ቃል
ጠብቆ ለማግኘት ይሕ ብቻ ይበቃል።
በጥቁር ሰማይ ስር ተወርዋሪ ኮከብ
በጨለማው መሓል ታይታ 'ማትጠገብ
በነዲድ በረኃ ሲጠፋ ጠብታ
ፈልቃ እንደምትጠጫት ለጥምሽ እርካታ
በረኃብ ዘመን ላይ ድንጋይን ቀይሮ
በሕልው አምላክ ቃል ለሕላዌ ኑሮ
እናም እልሻለሁ....
አንቺም እንደዚያ ነሽ...
ለሥጋና ነፍሴ ሙሴ መንገድ መሪ
በጨነቀኝ ሰዓት ባሕር አሻጋሪ!
15/04/09
2፡00
.@amehasilassie
አያቴ ሲነግረኝ፥
"ድንጋይ እንደ ዳቦ እየተቆረሰ፤
የአዳም ዘር በሙሉ ከመናው አፈሰ፤
በቀደመው ዘመን፥ እግዚአብሔር ሲመለክ በሕገ ልቦና
የእስራኤል አምላክ፥ ሕዝቦችን ሊመግብ ከፀሐይ ሰማይ ላይ
አውርዷል ደመና።
.
በጨለመው ሌሊት ይነጋ ማይመስል
እንዲሕ አስባለሁ አንቺን አምሰለስል
ምንድነው መናውስ ምንድነው ሰማዩ
የወረደላቸው በዐይናቸው ዕያዩ፤
እንኳንስ መቀየር ድንጋዩን ወደ ሕብስት
ላመነ ይቻላል አምላክ ቃሉን አይስት...
.
"ላመነ ይቻላል!" እልሻለሁ እኔም በተከበረ ቃል
ጠብቆ ለማግኘት ይሕ ብቻ ይበቃል።
በጥቁር ሰማይ ስር ተወርዋሪ ኮከብ
በጨለማው መሓል ታይታ 'ማትጠገብ
በነዲድ በረኃ ሲጠፋ ጠብታ
ፈልቃ እንደምትጠጫት ለጥምሽ እርካታ
በረኃብ ዘመን ላይ ድንጋይን ቀይሮ
በሕልው አምላክ ቃል ለሕላዌ ኑሮ
እናም እልሻለሁ....
አንቺም እንደዚያ ነሽ...
ለሥጋና ነፍሴ ሙሴ መንገድ መሪ
በጨነቀኝ ሰዓት ባሕር አሻጋሪ!
15/04/09
2፡00