.
በሚል ርዕስ አጠር ያለ የጥናት ጽሑፍ ለማዘጋጀት - - ከተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች
ጋር ቃለመጠይቅ እና የቡድን ውይይቶች ለማካሄድ ተነሳሁ፡፡
.
.
ለውጤታማ ጥናት መሠረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች ቀዳሚው ርዕሱ በመሆኑ ርዕሴን
ለማጥበብና ለማሻሻል ደጋግሜ አየሁት፡፡
.
የሚል ያልተገደበ ርዕስ ማንሳቴ . . .
በሚኒስቴር ደረጃ ተቀምጠው ከመሬት እስከ ግብር ከሚዘርፉት እስከ . . .
በየደጀሠላሙ እስከሚቀመጡ ነዳያን እንደ ናሙና ማንሳት ሊኖርብኝ ሆነ፡፡
.
በዛ ላይ ከመስርያቤት እስከ ጎረቤት ፣ (የሰፈሬ ባለሱቅ ሬድዋን ሳይቀር) የብድር
ደንበኛ መሆኔ ትዝ ሲለኝ ሽምቅቅ ብዬም ነው (የመስርያ ቤቴን የገንዘብ ቁጠባ
ማሕበር ራሱ የተቀላቀልኩት "ብድርና ቁጠባ" ስለሚል . . . በኢንግሊዙም 'ክሬዲት
አሶሴሽን' ስለሚል ለዛው የመበደር አመሌ ነው፡፡ ስለዚህ
.
.
እናም አሻሻልኩት ወደሚል ላጠበው ወሰንኩ፡፡
ፓ! አገኘሁት!
.
.
በቃ - በቴሌቪዥን ከሚደረጉ እርጥባኖች በፌስቡክ እስከሚደረጉ "ልመናዎች" ልተነትን
አሰብኩ፡፡ (ከዚህ በፊት 'ቅፈላ 101' በሚል መጽሐፍ ላሳትም ሞክሬ የቅፈላ ቴክኒኮችን
አጠያይቄ. . . በበቂ መጠን ባለማግኘቴ አለመሳካቱን አስታውሱ)
.
.
ኤኒዌይስ . . ብዬ
አሳጥሬው ተንቀሳቅሻለሁ. . .
.
.
☞ ድሮ 'ለልማት' እና 'ለሆስፒታል' ይባሉ እንደነበሩት ቴሌቶኖች 'ለአርቲስቶች' እና
ለግለሰቦች የሚደረጉ ገንዘብ ማሰባሰብያዎችን ዋቴቨር' እንዲል ኢንግሊዝ 'ምድረ
ለማኝ' ብዬ አልፌአቸዋለሁ፡፡
(በነገራችሁ ላይ 'የሃበሻ ወግ' መጽሔት የትላንት ዕትማቸው ላይ
# ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ቢራ_የሃገራችን_ኪነጥበብ_ምሰሶ ! በሚል ርዕስ ያወጡት አራት ገጽ
ሐተታም በየበዓሉ ላይ 'ስለ-ዐውዳመት' ተብሎላቸው በሺዎች 'የተቦጨቀላቸው' - -
"አርቲስቶች" ታሪክ ተዘርዝሯል)
.
.
ቀልዱስ ቀልድ ነው
እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን ግን ልመና በደማችን የተሰጠን ያህል ነውር ያጣነው
ለምንድነው??
.
በፊት በፊት እዚህ ፌስቡክ ላይ 'መጽሐፍ ላሳትም ብር አጠረኝ' በሚል ሰበብ ብዙ
ገንዘቦች 'ተቀፍለው' ነበር (በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ ከሚኖሩት)
.
ከዛ ቀጠለና የታመሙ፣ የተሰበሩ፣ የተቀነጠሱ ሰዎችን ፎቶ መለጠፍና 'ቡክ ከፍተናል'
መ'ባል ተጧጧፈ፡፡ 'ተቀፈለ' (በርግጥ ሁሉም ላይሆኑ ይችላሉ)
.
.
በውስጥ ለውስጥ በሚጧጧፉት
- የጅንጀና ፣
- የ"ታምሜአለሁ - የደክሜአለሁ"
- የ"መማርያ ጎደለኝ"፣
- የ"ካርድ ላኩልኝ" ፣
- የ"አጎቴ ወድቆ ተሰብሮ" ፣
- የ"ዲስኬ ተንሸራቶ"፣
- "በዚህ ገብቶ በዚህ ወጥቶ" . . . ልመናዎች እንዳሉ ሆነው . . . (ያው አምልጠው
ከምንሰማቸው 'ከባባድ' ማጭበርበሮች ውጪ)
ብዙዎቻችን በመለመን እና የሰውን ገንዘብ ለመቀበል በመሟሟት ላይ እንገኛለን፡፡
.
.
'ለምን' ብዬ የጅል ጥያቄ አልጠይቅም፡፡ ከጥቂቶች በቀር ብዙዎቻችን ስግብግቦች
ስለሆንን ነው፡፡ ከዛም በላይ ስንፍናችን ከሞራል ውጪ እንድንሆን ስላደረገን ነው፡፡
እንጂኮ ያልሰሩትን ያልለፉበት መጠቀም ነውር ነው፡፡ (አንዳንዱ ሚስቱን ልጁን እህቱን
ወይ ገርሉን ለባዕድ ገብሮ - ወላድ ላም ገዝቶ እንደሚያልብ ሰው እግሩን ዘርግቶ
ይበላል፡፡ አፈር ይብላ!)
.
.
በቃ እንደ ደህና ስራ . . .
- አንዳንዱ ለሱሱ - አንዳንዱ ለሚቀያይረው ልብሱ፤
- አንዳንዱ ቢጨንቀው እየተሳቀቀ - አንዳንዱ ቤቱ ተጋድሞ እየዋለ ደረቱን ነፍቶ
ያለሃፍረት፤
.
.
ብቻ ፍላጎታችንን እና አቅማችንን ስለማናመጣጥን ክብራችንን ጥለን ሰውንም
አስጨንቀን ኑሮ አይሉት ኑሮ 'እንኖራለን'፡፡ በየመንገዱ ስለሚወድቁት መነሳት መጨነቅ
የሚ'ገባን - - - ግን በየስልኩና በየኢንቦክሱ እየወደቅን እንነሳለን፡፡ ቅሌታሞች ነን፡፡
.
.
እጅ ተዘርግቶ ሲሆን እና ምላስ ተዘርግቶ ሲሆን ስሙም ስሜቱም ስለሚለያዩ እንጂ -
ልመና ልመና ነው - - - ለማኞች!!
ለምትሰሩ መልካም የስራ ሣምንት!
.
©ስመኝ ታደሰ ዘውዴ