ውድቀት ፥ ድርቀት ጠራኝ
.
#ረድኤት_አሰፋ
.
.
ለስንት ዐስርት ጥምቀት፥
ለስንት ዐስርት ገና፥ ድፎ የጋገረ
ከጎጆሽ ደጃፍ ላይ ፥
ያለው የኮባ ዛፍ ፥ ምን ነካው ጠቆረ?
አጉል ሰይፈነው ፥
"ይደርቃል" እያሉት፥ ሙሽራ ቅጠሉ ፥እንዳላንሰራራ
ምን ብትፈጽሚበት ?
ምኑ ላይ ብትቆርጪው፥ዳግም ማፍራት ፈራ?
.
.
አጥርሽስ ምነው ?
ዶፍና በረዶ ዓውሎ ሳይበግረው
ከታመመ አዛውንት ፥
አፍንጫ የወጣ ፥ ትንፋሽ ገነጠለው?
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል!
.
.
የጥንድነት ኑሮ ፥በጭስ ልትጀምሪ
የገና የጥምቀት ፥ዳቦ ስትጋግሪ
በምትቆርጪው ኮባ ፥ የተጠቀለለ
እንደ አብሮ መብላት ፥ አብሮ ማደር ያለ፤
እንደ ጎጆ ወጪ.. የወጣቶች ትዳር
ወላጅ በሌለበት፥ ዓመት-በዓል ለማክበር
እንደእናትሽ ልማድ ፥ እንዳ’ባቶቼ ወግ
እንደሚስት ዶሮ ፥እንደባል ሙክት በግ፤
የመጠጥ የምግቡ፥
የዘፈን ጭፈራው፥ የእንግዳው ብዛት
ያቆመን ተስፋችን ፥ ብሩሕ መልካም ምኞት
የመጀመሪያዬ ...
የመጀመሪያሽ ሰልፍ፥ የትዝታ መዓት!
በምትቆርጪው ፥ኮባ የተጠቀለለ
ለካ ትዝታችን ፥
ይኼ ኹሉ "ነበር!"፥ ካ’ንቺም ጋራ አለ?
.
.
ያው ኮባሽ ይጮኻል
.
.
በማጭድ በቢላ ፥
ሲቀረደድ ኑሮ ፥ ቀለም ያልቀየረ
ስትንከባከቢው፥
ስትኮተኩቺው ፥ እንደምን አረረ?
ለስንት ዐስር ጥምቀት
ለስንት ዐስር ገና ፥ ታርዶ ያላለቀ
ምን ቀረብኝ ብሎ ፥ ላይጸድቅ ደረቀ?
.
ሳርና ሰንደዶ፥ በቆመበት ዓለም
አጥርሽ ወደቀ፥ ምሳሌ ነው ይሔም፤
.
.
ዶፍና በረዶ ፥አውሎ ሳይበግረው
ከታመመ አዛውንት ፥
አፍንጫ የወጣ ፥ ትንፋሽ ያፈረሰው
አልገባሽም እንጂ ፥
እንደኮባው ኹሉ ፥ ያ'ጥሩም ጩኸት ነው!
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል!
.
.
የሁለት ልቦች ወግ ፥ የጥንድነት ቋንቋ
በወጪና ወራጅ ፥
ባ’ላፊና አግዳሚ ፥ ሸር እንዳይጠቃ
በገና በጥምቀት ፥
"ብሉልኝ!" "ጠጡልኝ!" ፥ የጎተተው መንጋ
እፍኝ ቆሎ ይዞ ፥
አሻሮ ለመዝገን ፥ እንዳይጠጋጋ፤
.
ሽተውሽ፣ ሽተዉኝ ፥ ከሩቅ የሚጣሩ
ለዓለም ስለሞትን፥
እንዲታወቃቸው ፥ሙት እንዳፈቀሩ
በግዑዝነቱ ፥
በበድንነቱ፥ በመተሳሰሩ
ልብሽና ልቤን ፥
ተክቶ የቆመ ፥ዋስ ነበር አጥሩ!
.
.
ስንደዶ እየቆመ ፥ ሳር እየጸደቀ
ምን ነክቶት አጥሩ፥
አውሎ ዶፍ በረዶ፥ሳይነካው ወደቀ?
.
.
ያው ኮባሽ ይጮኻል ፥
ምንም ሳይጎልበት ፥ አንዳችም ሳያጣ
ስውር ያፈንሽውን ፥
የናፍቆት ፍቅርሽን፥ በረንዳ ሊያሰጣ
ልብሽን ቀርቅረሽ ፥
አፍሽን ለጉመሽ ፥ በተደበቅሽበት
ያው ኮባሽ ይጮኻል ፥ በድርቀቱ አንደበት
ስለጎደለብሽ፥ እንደጎደለበት!
.
.
እስኪ አስቢው ላ’ፍታ
ከተቆለለበት የመደብ ከፍታ
ምድር ሳትናወጽ፥ ወይ ነፋስ ሳይንጠው
እንዴት በምን ስሌት ፥ መሬት ይመርጣል ሰው?
እስኪ አስቢው እንደው?!?!
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል ፥ ለኔም ቀናኝ ዛሬ
እገሰግሳለሁ ፥ ጩኸትሽን አክብሬ!
.
.
ኮባሽ አስተዋይ ነው ፥ ይናገራል ደርቆ
አጥርሽ ብልሕ ነው ፥ ይናገራል ወድቆ
ጩኸትሽን አሰማኝ ፥ከጉሮሮሽ ነጥቆ!
.
.
ለካ አልረሳሺኝም!?!?!
.
#ረድኤት_አሰፋ
.
.
ለስንት ዐስርት ጥምቀት፥
ለስንት ዐስርት ገና፥ ድፎ የጋገረ
ከጎጆሽ ደጃፍ ላይ ፥
ያለው የኮባ ዛፍ ፥ ምን ነካው ጠቆረ?
አጉል ሰይፈነው ፥
"ይደርቃል" እያሉት፥ ሙሽራ ቅጠሉ ፥እንዳላንሰራራ
ምን ብትፈጽሚበት ?
ምኑ ላይ ብትቆርጪው፥ዳግም ማፍራት ፈራ?
.
.
አጥርሽስ ምነው ?
ዶፍና በረዶ ዓውሎ ሳይበግረው
ከታመመ አዛውንት ፥
አፍንጫ የወጣ ፥ ትንፋሽ ገነጠለው?
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል!
.
.
የጥንድነት ኑሮ ፥በጭስ ልትጀምሪ
የገና የጥምቀት ፥ዳቦ ስትጋግሪ
በምትቆርጪው ኮባ ፥ የተጠቀለለ
እንደ አብሮ መብላት ፥ አብሮ ማደር ያለ፤
እንደ ጎጆ ወጪ.. የወጣቶች ትዳር
ወላጅ በሌለበት፥ ዓመት-በዓል ለማክበር
እንደእናትሽ ልማድ ፥ እንዳ’ባቶቼ ወግ
እንደሚስት ዶሮ ፥እንደባል ሙክት በግ፤
የመጠጥ የምግቡ፥
የዘፈን ጭፈራው፥ የእንግዳው ብዛት
ያቆመን ተስፋችን ፥ ብሩሕ መልካም ምኞት
የመጀመሪያዬ ...
የመጀመሪያሽ ሰልፍ፥ የትዝታ መዓት!
በምትቆርጪው ፥ኮባ የተጠቀለለ
ለካ ትዝታችን ፥
ይኼ ኹሉ "ነበር!"፥ ካ’ንቺም ጋራ አለ?
.
.
ያው ኮባሽ ይጮኻል
.
.
በማጭድ በቢላ ፥
ሲቀረደድ ኑሮ ፥ ቀለም ያልቀየረ
ስትንከባከቢው፥
ስትኮተኩቺው ፥ እንደምን አረረ?
ለስንት ዐስር ጥምቀት
ለስንት ዐስር ገና ፥ ታርዶ ያላለቀ
ምን ቀረብኝ ብሎ ፥ ላይጸድቅ ደረቀ?
.
ሳርና ሰንደዶ፥ በቆመበት ዓለም
አጥርሽ ወደቀ፥ ምሳሌ ነው ይሔም፤
.
.
ዶፍና በረዶ ፥አውሎ ሳይበግረው
ከታመመ አዛውንት ፥
አፍንጫ የወጣ ፥ ትንፋሽ ያፈረሰው
አልገባሽም እንጂ ፥
እንደኮባው ኹሉ ፥ ያ'ጥሩም ጩኸት ነው!
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል!
.
.
የሁለት ልቦች ወግ ፥ የጥንድነት ቋንቋ
በወጪና ወራጅ ፥
ባ’ላፊና አግዳሚ ፥ ሸር እንዳይጠቃ
በገና በጥምቀት ፥
"ብሉልኝ!" "ጠጡልኝ!" ፥ የጎተተው መንጋ
እፍኝ ቆሎ ይዞ ፥
አሻሮ ለመዝገን ፥ እንዳይጠጋጋ፤
.
ሽተውሽ፣ ሽተዉኝ ፥ ከሩቅ የሚጣሩ
ለዓለም ስለሞትን፥
እንዲታወቃቸው ፥ሙት እንዳፈቀሩ
በግዑዝነቱ ፥
በበድንነቱ፥ በመተሳሰሩ
ልብሽና ልቤን ፥
ተክቶ የቆመ ፥ዋስ ነበር አጥሩ!
.
.
ስንደዶ እየቆመ ፥ ሳር እየጸደቀ
ምን ነክቶት አጥሩ፥
አውሎ ዶፍ በረዶ፥ሳይነካው ወደቀ?
.
.
ያው ኮባሽ ይጮኻል ፥
ምንም ሳይጎልበት ፥ አንዳችም ሳያጣ
ስውር ያፈንሽውን ፥
የናፍቆት ፍቅርሽን፥ በረንዳ ሊያሰጣ
ልብሽን ቀርቅረሽ ፥
አፍሽን ለጉመሽ ፥ በተደበቅሽበት
ያው ኮባሽ ይጮኻል ፥ በድርቀቱ አንደበት
ስለጎደለብሽ፥ እንደጎደለበት!
.
.
እስኪ አስቢው ላ’ፍታ
ከተቆለለበት የመደብ ከፍታ
ምድር ሳትናወጽ፥ ወይ ነፋስ ሳይንጠው
እንዴት በምን ስሌት ፥ መሬት ይመርጣል ሰው?
እስኪ አስቢው እንደው?!?!
.
.
ምሳሌ ይቀናሻል ፥ ለኔም ቀናኝ ዛሬ
እገሰግሳለሁ ፥ ጩኸትሽን አክብሬ!
.
.
ኮባሽ አስተዋይ ነው ፥ ይናገራል ደርቆ
አጥርሽ ብልሕ ነው ፥ ይናገራል ወድቆ
ጩኸትሽን አሰማኝ ፥ከጉሮሮሽ ነጥቆ!
.
.
ለካ አልረሳሺኝም!?!?!